ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኤርትራ ድንበር አካባቢ በጥበቃ ላይ የሚገኙ ወታደሮች በመረጃ ስህተት ለ33 ዲቃዎች በባዶ ሜዳ ላይ ሲተኩሱ የዋሉ ሲሆን፣ ለጦሩ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት መከላከያን አወናብደዋል የተባሉ 5 ወታደሮች ተይዘው እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ከግንቦት ሰባት ተኩስ ተከፈተ ተብሎ ለማዕከላዊ የጦር ሃይል ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ይህን ተከትሎ ከፍተኛ መደናገጥ ተገብቶ እንደነበር ከኢህአዴግ የፖለቲካና የደህንነት ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሁሩሶ እና የብርሸለቆ መሰረታዊ የወታደር ማሰልጠኛ ማዕከል በተደረገ ውይይት ተወያዮች አገሪቱ በብሄር ስርዓት ተኮር እየተመራ ነው፣ በስልጠና መምሪያ ያለው የህውሃት የአመራር የበላይነት ከኢትዩጵያ ወታደርነት ይልቅ የህውሃት ጠባቂነት የሰፈነበት ሁኖ አግኝተነዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
የስልጠናው ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ገ /እግዚብሄር በመሩት የስልጣኞች የመልካም አሰተዳደር መድረክ ላይ ሰልጣኞቹ ፤ “ከአንድ ቤተሰብ ሶሰት እና ሁለት ልጆች የመጣነው በስራአጥነት ነው፣ ከዚህ ከመጣን በኃላ ከሁለት ትንንሺ ዳቦ እና ምስር በስተቀር ሌላ ምግብ አይቀርብልንም፣ በረሃብ እየሞትን ነው፣ ብለዋል፡፡
ሰልጣኞች ከታራሚ እስረኛ ያነሰ የ7 ብር የቀን አበል ብቻ እንዴት ይከፈለናል ሲሉም ጠይቀዋል። sourse esat radio
No comments:
Post a Comment