Wednesday, January 8, 2014

የኢትዮጵያ ትምህርት አደረጃጀት ጋጋታ ለዉድቀት ወይስ ለጥራት!

Wednesday, January 8, 2014 @ 05:01 PM ed
ባይለ ደራሽ ምህረቴ
ምህርት ሚኒስተር በ1ኛና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ የመማር ማስተማሩን ሂደት በጥራት ለማከናወን ይረዳል በሚል ስበብ በየግዜዉ የሚፈበረኩ የአደረጃጀት ኩልኩሌ /ጋጋታ/ በማምጣት መምህራንን፤ተማሪንና ወላጅን ከማስጨነቅ አልፎ የትምህርቱን ጥራት ከመቸዉም በላይ እየዘቀጠ እንዲሄድ አድርጓል። ለዚህ መረጃ ይሆን ዘንድ ዓለም ባንክ በዲሴበር 7/2012 በ221 ገጽ በዘጠኝ ምዕራፍ በሰጡት መግለጫ አንኳር ነገሮችን አንስተዋል። እነዚህም አንኳር ጉዳዮችን በሰፊዉ በማተት የችግሩን አሳሳቢነት በማጉላት መንግስት በአስቸኳይ ርምት መዉሰድ እንዳለበት በአንክሮ ያስጠነቀቀ ሲሆን ችግሩንም በአፈጣኝ መግታት ካልተቻለ በአገርና በህዝብ ላይ ለያመጣ የሚችለዉን ችግር በግምገማዉ አስቀምጧል።
ኢህአደግ በየግዜዉ አዳዲስ የአደረጃጀት ጋጋታ በማምጣት ከመምህራንና ከተማሪዎች ጋር ግብግብ ሲፈጥር ይታያል እነዚህም አዳዲስ የትምህርት አደረጃጀቶች፡-የትምህርት ጥራትፓኬጅ፤ ኮማንድ ፖስት፤አንድ ለአምስት፤BPR/መሰረታዊ የስራ ሂደት፤የመምህራን ዉጤት ተኮር፤የልማት ሰራዊት፤ታህድሶ ፤የለዉጥ ሰራዊት፤ተማሪን ያማከለ የማስተማር ሂደት፤ሪፎርሜሽን/Reformation/…,የመሳሰሉትን የአደረጃጀት ኩልኩሌ/ጋጋታ/በማምጣት በትምህርቱ፤ በመምህራንና በተማሪዎች ዘንድ መቀቃርን በመፍጠር በትምህርት ዘርፉ ላይ ግዙፍ የጥራት ኪሳራ አሳይታል።እኔም ከዚህ በላይ የጠቀስኋቸዉን/የተጠቀሱትን የአደረጃጀት ጋጋታዎች በመዳሰስ አዎንታዉና አሉታዊ አካሄዳቸዎን ለማስቀመጥ እሞክራለሁ።
1/ የትምህርት ጥራት ፓኬጆች በአምስት ዋናዋን ክፍሎች ይከፈላሉ
ሀ/ የትምህርት ቤት መሸሻል መርሃ ግብር፡-ምቹ፤የተዋበና ለመማር ማስተማሩ ማራኪና የተዋበ ማድረግና
የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጎልበት ነዉ።
ለ/ የመምህራን ልማት መርሃ ግብር፡-የመምህራንን አመለካከት መለወጥ፤የመምህራንን አቅም ማሳደግና አዳዲስ
አሰራሮችን በመምህራንና በባለሙያዎች በማስጠናት ለትምህርቱ እድገት የሚበጁትን አሰራሮች መተግበር።
ሐ /የኢንፎርሜሽንን ቴክኖሎጅ ማሻሻያ መርሃ ግብር፡-መምህራንና ተማሪዎችን ከዘመኑ መረጃና እዉቀት ጋር
ማስተዋወቅና በዚሁ መርሃ ግብር በመጠቀም እዉቀታቸዉን ማሳደግ።
መ/  የስነ ዜጋና ስነምግባር ትምህርት መርሃ ግብር፡-የሀገሪቱን ህገ መንግስት ማዉቅና ለተማሪዎች በማስረጽ
የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብም በእኩልነት ላይ፤ በማንነት ላይ፤በህግ የነላይነት ላይ በመሳሰሉት ላይ የነቃን
የበሰለ ግንዛቤ መዉሰድ።
ሠ/  የስርዓተ ትምህርት መርሃ ግብር፡-ስርዓተ ትምህርቱን በመፈተሽ ግድፈቶችን አስወግዶ የማሰተካከል እርምጃ
መዉሰድ፤ተማሪዎችን ያሳተፈና ክህሎታቸዉን በሚያዉጣ መንገድ ማሰተማር፤የተማሪዎች ዉጤት
የሚሸሻልበትን መንገድ መተለም፤ተማሪዎችን ሊመዝንና የባህሪ ለዉጥ ሊያመጣ የሚችል መንገድ መተለም።
ረ/  የትምህርት አደረጃጀትንና አሰራር ማሸሻያ መርሃ ግብር፡-የትምህርት አስተዳደር ከማነኛዉም የፖለቲካ
አስተሳሰብ በመዉጣት መምህራንና ተማሪዎችን በማቀራረብ የትምህርቱን ስራ ለማጎልበት ወቅታዊ
አሰራሮችን መተግበር።
ከዚህ በላይ የጠቀስኋቸዉ ሳይንሳዊ ትንታኒያቸዉ ሲሆን ኢህአድግ እየተጥቀመበት ያለዉ በጠረጴዛዉ ገጽ ላይ እነዚህ ያማሩና አለም አቀፍ አደረጃጅቶችን በማስቀመጥ የጠረጴዛዉን ዉስጥ/under the table/የራሱን የፖለቲካ ማራመጃና ማስፋፋያ በማድረግ የሃገሪቱ ትምህርት እንደፋሽን በፈለገዉ ግዜ በመቀያየርና በመጫን የትምህርቱን ጥራት በእጅጉ ጎድቶት ይገኛል።
2/ ኮማንድ ፖስት፡-ት/ቤቶችን ከህዝብና ከመንግስት ክንፎች ጋር በማስተባበር መማር ማስተማሩን ሴኩላር በማድረግ ትምህርቱ የሚጎለብትበትንና ጥራቱ ጠብቆ የሚሄድበትን መንገድ መተለምና መተግበር ሲሆን መንግስትእየተጠቀመበት ያለዉ አሉታዊ የአደረጃጀት መምህራን ዋናዉን ጉዳይ በመርሳት መንግስት በሚሰጣቸዉ የአሉታዊ አደርጃጀት ኩልኩሌ በመጠመድ ከትምህርት ጥራት ወደ ሪፖርት ጥራት ተሽጋግሯል።
3/ አንድ ለአምስት፡- ተማሪዎችን በቡድን በማደራጀት ማህበራዊ ግንኙነታቸዎን በማጎልበት አብሮ የመስራትና የመተሳሰብ ክህሎታቸዎን ማሳደግ ሲሆን ገዥዎ መንግስት እየተጠቀመበት ያለዎዉ በቡድኑ ዉስጥ የራሱን አባሎች በመመደብ የራሱን የፖለቲካ አቋም የማይደግፉትን በመለየትና በተለያየ መንገድ ተማሪዎችን በማሸማቀቅ አልፎዎም የቤተሰቦቻቸዎን የፖለቲካ አቋም መገምገሚያ ሲሆን ይታያል።
4/ BPR/Business process reengineering/መሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ:-
  • አንድን ድርጅት ወይም ተቋም ለዉጥ ሊያመጣ የሚችልበትን የሰዉ ሀይል ግንባታ ለትምህርቱ ለዉጥ ሊያመጡ የሚያስችሉትን/ኮፒተር፤ICT፤ቤተሙከራ፤ቤተመጽሐፍት፤ትምህርት ማበልጸጊያና የመማሪያ ቁሳቁሶችን ግባት በማሟላት በትምህርት ቤቱ/በተቋሙ/ ዉስጥ በሚገኙት ሰራተኞች ፍላጎትና እምነት መሆን አለበት።
  • መልካም አስተዳደር በማመቻቸት የትምህርቱን ጥራትና ዉጤት የተሻለ ደረጃ ማድረስ
  • ሜዛናዊ የመምህራን ዉጤትተኮር አስራር ማስፈን
  • የመምህራንና የተማሪዎችን ቅሬታ አግባባዊ በሆነ መንገድ መፍታት
  • በሙያዉ ብቁ የሆኑና ግልጸኝነትን የተላበሱ አመራሮችን መመደብ
  • የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ
  • የሰራተኞችን እዉቀትና ክህሎት መጨመር
  • ተጨባጭ ለዉጥ ሊያመጣ የሚያስችል ጥናት በሙያተኛዉ በማስጠናት ዉጤቱን በሚያስጠብቅ መንገድ መተግበረ
  • ለመምህራን የማትጊያና የማበረታቻ ስራዓት በመዘርጋት የትምህርቱን ጥራት ማጎልበት
ከላይ በአንኳርነት የጠቀስሗቸዉ በትምህርቱ ስርዓት ዉስጥ በመሰካት ትምህርቱን በማጎልበት የሚገኙ ሲሆን የኢህድግ መንግስት የአደረጃጀት ጋጋታ በመፍጠር መምህርንና ተማሪዎችን በማቃቃር ሀገሪቷ ትምህርትን ካልተጠቀሙበት ሀገር አንዷ ሆናለች።
ለዚህ ጉልህ ማሳያ የሚሆን ወያኔ በትግራይ ክልል መማር ማስተማርን በተመለከተ አንድ ማሳያ ማቅረብ እፈልጋለሁ።
በመቀሌ ከተማ መቀሌ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጅና ቀዳሚኖ 1ኛና 2ኛ ደረጃ /ቤት አድሀሪ የሆኑት
  • ዉስጥ አደረጃጀታቸዉ የአዉሮፓንና የአሜሪካን ስታንደርድ የያዙ
  • መምህራን በዉጭ ሀገር መምህራንና በሙያዉ ከፍተኛ ብቃት ያላቸዉ
  • የተማሪዎች ቅበላ ከትግራይ ብቻ የሆነ
ሲሆን ተማሪዎች ትምህርታቸዉን በሚጨርሱበት ጊዜ በኢትዮጵያ ባሉ ቁልፍ መስሪያቤቶች ያለምንም ዉድድርና ማስቲዎቅያ  የተለየ እስኬል በማስቀመጥ በቀጥታ ሲመደቡ የተቀሩት በዉጭ ሀገር በሚገኙ እንባሴዎችን በሀገር ዉስጥ የስለላ መረቡን ተብትበዎ ይገኛሉ የተቀሩት ደግም በእንግሊዝን ፤ በአዉሮፓና በአሜሪካ በመንግስት ልዩ ትእዛዝ ለከፍተኛ ትምህርት ይላካሉ።መንግስት /ወያኔ/ ህገመንግስቱን ከሽኖ በወረቀት በማስቀመጥ ዉስጥዉስጡን የሚሰራዉ ገሀዱ ይህ ነዉ።ለዚህ አፍራሽ ተግባር ሁላችንም በመረባረብ የሁሉም ክልል የትምህርት አሰጣጥ ፍታዊነቱን ማረጋገጥ አለብን።              ምንጭ አዲስ ቮውይስ

No comments: