Sunday, October 20, 2013

ያሇም አቀፉ ወጀሌ ፍርዴ ቤት ምስክር


ፕሮፌሰር ዓሇማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ሇሃገሬ

የስሱ ብርጌዴ የዯቦ ፍርጠጣ ጥረት
የአፍሪካ አንዴነት (እኔ ሇማስረዲት የተገዯዴኩበት አሳፋሪው ከሮም ስምምነት ፍርጠጣ) ‹‹የዯቦ የማስፈራራት ሕብረት›› ከሸፈ፡፡
‹‹አሰቸኳዩ ሌዩ ስብሰባ›› ‹‹አ አ ከዓሇም አቀፍ የወንጀሇኞች ችልት ጋር ያሇው ግንኙነትያከትማሌ ብሇው ያሰቡትና ሴራውን የፈተለት
ባሇስሊጣናት፤ ‹‹ከተባበሩት መንግስታት የፀፅታ ካውንስሌ ጋር ውይይት ሇማዴረግ በሚሌ እሳቤ በኬንያው ፕሬዜዲንትና ምክትሌ
ፕሬዜዲንት እንዱሁም በሱዲኑ ፕሬዜዲንት ሊይ የተመሰረተውን ክስ በተመሇከተ አፍሪካ አንዴነት ሌዩነት አሇው፤ የሮም ስምምነት
አንቀጽ 16 እነሱን ተጠያቂ ሉያዯርጋቸው ኣይገባም ምህረት ያዴርግሊቸው አይነት ውሳኔ ይዞ መጠናቀቁ አስገርሟቸዋሌ፡፡
እንዯፈራሁትም ኦክቶበር 11-12 2013 ስብሰባም አሳፋሪ ሆኖ በታሪክአይኖርም፡፡ 34ቱን የሮም ስምምነትን የፈረሙትና የአፍሪካ
ሃገራት አሳምኖ የፍርጠጣ ማስፈራራያውን ተግባራዊ ማዴረጉ የዯቦ ጥረት በጠቅሊሊው ከሽፏሌ፡፡ በብዛት የሮም ስምምነትን ጥሇን
እንወጣሇን የሚሇው ማስፈራሪያ የጨረባ ተዝካር ሆኖ ቀርቷሌ፡፡ የገዢው ፓርቲ አባሊት ሃይሇማርያምዯሳሇኝና ቴዎዴሮስ አዴሃኖም
ያወናከሩት ሴራቸው ማንም ሳይቀበሇውቀረ፡፡ ሇዚሁም መሰናከሌ አዴሃኖም መገናኛዎችን መጥፎ መሌእክት አዛዮች ሲሌ ወነጀሊቸው፤
‹‹አንዲንዴ መገናኛዎች ተከፋፍሇዋሌ ይሊለ እኛ ግን አንዴም የዚያ አዝማሚያ የሇንም: ያሇን አንዴ ምርጫ አንዴነታችንን መጠበቅ
ነው›› ብል ነበር፡፡
በአንዴ ጎኑ አዴሃኖም እውነት አሇው፡፡ 34ቱ የሮም ስምምነት ፈራሚዎች በእነ ሃይሇማርያም የተሸረበውን የዯቦ ፍርጠጣ ሊሇመቀበሌ
በአንዴነት ጸንተው ምርጫቸው በአንዴነት መቆም መሆኑን አረጋግጠዋሌ፡፡ ብቻቸውን መሃሌ ሜዲ ቀርተው ከሮም ስምምነት እንውጣ
ብሇው ነጭ ባንዱራቸውን በማውሇብሇብ የባረቀባቸው መሌእክታቸው ጋር የቀሩት ሃይሇማርያምና አዴሃኖም ብቻ ነበሩ፡፡ አንዴም
ፈራሚ ሃገር በአይ ሲ ሲ (ያሇም አቀፉ ወጀሌ ፍርዴ ቤት) እንውጣ የሚሇውን ሃሳብ ዯግፎ የወገናቸው አሌነበረም፡፡ የአፍሪካ
የስምምነቱ ፈራሚ ሃገራት የሮም ስምምነት ሇአፍሪካ መሪዎች እንዯማይስማማና መጣሁብህ ካሊረፍክ፤ ችልትእግርሃሇሁ እንጂ ሕዝብን
እየበዯሌክ አትቀጥሌም በማሇት መሪዎቹን ቢያስጠ ነቅቃቸውም አይ ሲ ሲ ሇአፍሪካ ሕዝቦችዋስ ጠበቃቸው እንዯሆነ በሚገባ
ተገንዝበዋሌ፡፡ በሌዩ አስቸኳይ ስብሰባው የነበረው ከሕግ የመፈርጠጡ ማስፈራሪያ ከንቱ ነውና፤ የአይ ሲ ሲ ተግባር ይቀጥሊሌ፤የሩቶና
የተባባሪዎቹ ክስ መታየቱ ይቀጥሊሌ፡፡ የኬንያታ ችልት ሂዯት በኔቬምበር 12 መሰማት ይጀምራሌ፤ ባሺርም ከዓሇም አቀፍ ፍትህ
ማስገዯጃው እንዯወጣበት ኮብሊይነቱ ቀጣይ ይሆናሌ፡፡
የፍርጠጣ ሕብረት አዴርባይነት፡ አዯገኛ የጫጩቶች ጫጫታ
በኦክቶበር 11-12 2013 በአይ ሲ ሲ ሊይ የተካሄዯው የአፍሪካ አንዴነት አስቸኳይ ስብሰባ ችሊ ሉባሌአሇያም አናሳ ግምት ሉሰጠው
አይገባም፡፡ ሇምንነቱ ሉመሰገን ይገባዋሌ፡- ሇፍርጠጣ ሕብረት አዴርባይነቱ፡፡ ይህን አስቸኳይ ስብሰባ እንዱጠራ የወተወቱት የአፍሪካ
መሪዎች፤ ከሁሇተኘው ዓሇም ጦርነት ወዱህ የተቋቋመውን ብቸኛና ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ዓሇም
አቀፋዊ የፍትሕ ተቋም የጫጩ ሚጫወቱ ናቸው፡፡ሃሳባቸው34ቱን የአፍሪካ ፈራሚ ሃገራት በሽብር አውቶቡሳቸው አሳፍረው ከአይ ሲ
ሲ ጋር በማጋጨት አይ ሲ ሲንሇማስፈራራትና በመጨረሻዋ ሴኮንዴ ሊይ ፍሊጎታቸውን እንዯሚያሟሊ እርግጠኛ ሆነው ነበር በምኞት
ቅዠታቸው፡፡ዯግነቱ አይ ሲ ሲ በዓሊመውና በተቀበሇው አዯራ ጸንቶ ወይ ፍንክች ያባ ቢሊ ሌጅ አሇ፤ አውቶቡሱም
ባድውንከአሽከርካሪው ከሃይሇማርያም ዯሳሇኝና ከወያሊው ቴዎዴሮስ አዴሃኖም ጋር ያሇተሳፋሪ ቀረ፡፡ ተስፋ ቆርጠውበማሸብረክ አይ ሲ
ሲ ከሰብአዊ መብትን ከሚጥሱ ወንጀሇኞች፤ ከጦር ወንጀሇኞች ጋር፤ በዘር ሕዝብን ከሚጨፈጭፉትጋር፤ ተጎጂውን ሕዝብ
ሇማስማማት የሚችሌ ክበብ ሇማዯረግ በሚሌ እያጉረመረሙ የማይሰማና ተቀባይ ያጣ ሙሾ ማውረዴያዙ፡፡
አይ ሲ ሲን የማዯናቀፉ የእሌህ እሽቅዴዴም
የሃይሇማርያምና የቴዎዴሮስ አዴሃኖም አይ ሲ ሲን የማዯናቀፉ ጨዋታ ፕሊን 34 ቱ የሮም ስምምነት ፈራሚ ሃገራትን ፊት አዞረባቸው፡
፡ ሃይሇማርያምና አዴሃኖም በንግግራቸው ፈራሚ ሃገራትን ያሰባስብሌናሌ ብሇው ያሇሟቸውን በርካታ እቅድች አቅርበው ነበር፡፡ 1. በሥሊጣን ሊይ ያለ መሪዎች (ከሕግ በሊይ ይሁኑ:-ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አንዯሚባሇው ሁለ) የተጠያቂነት ከሇሊ ያግኙ፤ 2.
ያሇፈውን እንዲሇፈ አርገን እንርሳው፤ 3. አይ ሲ ሲ አፍሪካና አፍሪካውያን ሊይ ያተኮረ አስከፊ የፖሇቲካ ተቋም አሇው ፤4. 34ቱ
ፈራሚ ሃገራት ስምምነቱን ሲፈርሙ የነበራቸው ግናዛቤ ተቋሙ ያሇአዴሌዎና ፍትህን መሰረት ባዯረገ መሌኩ ስራውን ያከናውናሌ
በሚሌ እምነት ነበር፤ (ትክክከሇኛ አስተሳሰብ አሌነበረም)፤ 5. በኬንያታ ሩቶና በበሺር ሊይ የተመሰረተው ክስ ባገር ዉስጥ ያሇዉን
የመቻቻለን ሂዯት ያበሊሸዋሌ፤ 6. አይ ሲ ሲና የተባበሩት መንግስታት ሴኪውሪቲ ካውንስሌ ባሇሁሇት አዴሌዎ መሌክ ፍትህ ነው
የሚያሳዩት: አንደ ሇአፍሪካውያን ላሊው ዯሞ ሇላልች፤ 7. አይ ሲ ሲ አፍሪካውያንና አፍሪካን በዚህ ሁኔታ ሉመሇከትእንዯማይገባው
ሌናሳውቀው ይገባናሌ ነው:: አንዴ የስምምነቱ ፈራሚ ያሌሆነ ሃገር ‹‹መሪዎች›› (ማሇትም ኢትዮጵያ) እንዳት አዴርገው ስምምነቱን
አምነውና ተቀብሇው የፈረሙ ለአሊዊ መንግስታትን ሃገራት መሪዎችን እጅ በመጠምዘዝ ስምምንቱንና አይ ሲ ሲን አንቅራችሁ ትፉ
ረግጣችሁ ዉጡ በማሇት የሽብር ከበሮ ይዯሌቃለ ?
በስሌጣን ኮርቻ ሊይ ሇተፈናጠጡት የአፍሪካ መሪዎች ከወህኒ ማምሇጫ ካርዴ ይሰጣቸው ነው ያሇው አዴሃኖም በንግግሩ ሊይ በሰጠው
አስተያየት ‹‹የሃገር መሪዎች የስሌጣን ዘመናቸው እስኪያበቃ ዴረስ ከተጠያቂነት ነጻ ሉሆኑ ይገባሌ:: የሃገር መሪዎችን መክሰስና
መመርመር ሇኬንያና በአጠቃሊይም ሇአፍሪካ ትሌቅ ጉዲት አሇው::›› አዴሃኖም ሲማጸንም ‹‹ፍትሕን ማስከበሩ ዘሊቂ ማፍትሔ
ሇማስገኘት የሚዯረገውን ጥረት በማይጎዲ መሌኩ ሉሆን ይገባሌ›› በማሇት ተረት ተረት ይሇናሌ፡፡ አዴሃኖም ምርመራንና ክስን
በተመሇከተ ያነሳቸው አንዲንዴ ነጥቦች እውነትነት አሊቸው፤ ያሇአንዲች ቁጥጥር ሰብአዊ መብትን የገፈፉትን፤ የግፍ ጭፍጨፋ
ያካሄደትን፤ የዘር ግዴያን የተገበሩትን፤ አፍሪካንና አፍሪካውያንን በንቀት ሇመከራና ሇዴህነት የዲረጓትን ‹‹መሪዎች›› የአይ ሲ ሲ
አካሄዴ ምጥ ሉያስይዛቸው ይችሊሌ፡፡ የአሇም አቀፉ የወንጀሇኞች ፍርዴ ቤት ረጂሙ የሕግ እጅ በአፍሪካ የስሌጣን ወንበር ሊይ
የተኮፈሱትን የስብአዊ መብት ገፋፊዎች፤ በቤተ መንግስታቸው ተቀምጠው በአፍሪካና በአፍሪካውያን ሊይ የግፍ ጭፍጨፋ
የሚያካሂደትን በጫካ በነጻ አውጪ ስም ተሸሽገው ያለ ‹‹መሪዎችን›› ሽባ እንዯሚያዯርግ ግሌጽ ነው፡፡
እርግጥ ስምምነቱን ያሌፈረሙና ያሌተቀበለ እንዯኢትዮጵያ ያለት ሃገራት ያሇምንም ተመሌካችና ሃይ ባይ ያሻቸውን ኢሰብአዊ
ተግባራት ማከናወን፤ ንጹሃናን መግዯሌ፤ በዘር ሊይ የተመሰረተ ግዴያን ማካሄዴ፤ እንማራሇን የሚለትን ሃገርና ሕዝብ መበዝበዝ ይችሊለ
ማን አሇባቸውና! ከዚያም አሌፈው የዴፍረታቸው ዴፍረት አይ ሲ ሲን ሊማኮሊሸት አይ ሲ ሲ አፍሪካውያንን ሇይቶ የሚያዴን ተቋም
ነው በማሇት የሽብር ቅጥፈታቸውን ይነዛለ፡፡
ሇመሆኑ ሇምንዴን ነው በሥሌጣን ሊያ የተቀመጡት ‹‹መሪዎች›› ሰብአዊ መብትን ከጣሱ፤ የዘር ማጥፋትን ከፈጸሙ፤የጦር ወንጀሇኛ
ሆነው ከተገኙ የማይከሰሱት? አዴሃኖም እራሳችንንን ከክስ ሇማዲን የሚሌ የቅብጠት መሌስ ካሌሆነ በቀር ላሊ መሌስ አይኖረውም፡፡
ሰብአዊ ጥሰትን፤ የግፍ ግዴያን፤ የዘር ማጥፋትን ባስመሇከተ ይከሰሱ ከተባሇ መሪዎቹ ከክስ ሇማምሇጥ ሲለ በምንም መሌኩ ምርጫ
አካሂዯው መሸነፍን አይሞክሩትም:: ስሇዚህም አዴሃኖምና ሃይሇማርያምአሊማቸው በግፍ መንበረ ዙፋናቸው ሊይ እስከ እሇተ ሞታቸው
በሕግ ሳይጠየቁ ሇመወዘፍ ነው፡፡ የማይከሰሱት የማይገረሰሱትየማይዯፈሩት ዘሌአሇማዊ ሆነው ሇመኖር ነው፡፡ በጫካ ሇነጻነት ታጋይ
ነን የሚለትና በቀኝ በግራ ወንጀሌ በመፈጠም ሊይ ያለትም በበኩሊቸው እኛ የሕዝብ እንባ አዴራቂ ነንና የሕዝቡ እውነተኛ ተወካዮች
በመሆናችን ሌንከሰስአይገባንም ቢለስ ምን የሚያግዲቸው ዯንብ አሇና:: የሃይሇማርያምና የአዴሃኖም ሕግ እንዯሆነ
ወንጀሇኞችከነወንጀሊቸው፤ ከነጥጋባቸውና ንቀታቸው በስሌጣን ሊይ ሆነው አይከሰሱ ነው የሚሇው፡፡በዘር ፍጅት፣ በጦር ወንጀሇኛነት
ወይም ህዝብን በማሰቃየት ተሳትፈው ወይም አዘው የሚያስፈጁ እነዚህ የአፍሪካ አምባገነን ገዥዎች ስሇሆኑ እነሱ ቢገዴለ፣ ቢያስፈጁ
መብታቸው አዴርገውት መከሰስ የሇብንም ብሇው ሲጠይቁ ትንሽ እንኳን አሇማፈራቸው ያስዯንቃሌ፡፡ በ21ኛው ክፍሇ ዘመን ንጉስ
አይከሰስ ሰማይ አይታረስ የሚሇው የፊውዲሌ መዝሙር ቦታ እንዯላሇው እንዳት አያውቁም? በእርግጥ ሰማይ ሊይታረስ ይችሊሌ፣
በአውሮፕሊን መቀዘፉ እንዯ እርሻ ይቆጠራሌ ካሌተባሇ በስተቀር፡፡ ንጉስ ግን ሰው ነው፣ እንዯማንኛውም ሰው ተፀንሶ ተወሌድ አዴጎ
ነው ሇስሌጣን የበቃው፡፡ እንዯ ማንኛውም ሰው ዯግሞ ያረጃሌ፣ በመጨረሻም ወዯማይቀረው ዓሇም ይሰናበታሌ፡፡ዴሮ የሰው ሌጅ
ስሌጣኔ ገና ባሌዲበረበት ዘመን ንጉስ ከሊይ ተቀብቶ ታዝዞ የመጣ እንዯሆነ ስሇሚቆጠር የፈሇገውን ማዴረግ ይችሊሌ፣ አይከሰስም
አይወቀስም ይባሌ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ያፈጀ ያረጅ ነው፡፡ የሌዕሇ ኃያሎ አገር መሪ ኦባም ይወቀሳሌ ይከሰሳሌ፡፡ ሰሇዚህ
ይህ ሀሳብ ኢትዮጵያን የምታህሌ ታሊቅ አገር የሚመሩና የህብረቱ መቀመጫ የሆነችው አገር መሪዎች፣ መብትን ሇመግፈፍና
ሇመጨፍሇቅ ግንባር ቀዯም ሆነው ይህን ማሇታቸውአሳዛኝ ነው፡፡
የዘገየ ፍትሕ የተነፈገ ሕግ አሇያም፤ ኢፍትሏዊ ነው፡፡
በሌዩ አስቸኳይ ስበሰባው ሊይ ሃይሇማርያም ምስክርነት ሲሰጥ ‹‹በአይ ሲ ሲ የባሺር ክስ የተሇየ ሉሆን ይገባሌ ምክንያቱም አስፈሊጊውን
ፖሇቲካዊ አመራር በመከተሌና የዲርፉርን ችግር ሇመፍታት ቁርጥ ውሳኔ ሊይ በመዴረስ ከዯቡብ ሱዲንም ጋር ያሇውን አሇመግባባት ሇመቋጨት በመንቀሳቀስ ሊይ ነው፡› ይሊሌ:: በተመሳሳይም ኬንያታ እና ሩቶ ኬንያ አዱስ ሕገ መንግስት ያጸዯቀች በመሆኗ የእነርሱም
ክስ በተሇየ ሉታይ ይገባሌ፤ እንዱሁም በኬንያ የነበረውን ሁለ በመሇወጥ ሇሕዝቡና ሇሃገሪቱ› ታይቶ የማይታወቅ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ
እንዱካሄዴ አዴርገዋሌና፤ምስጋና ሉቸራቸው ይገባሌ ይሊሌ፡፡
ሃይሇማርያም በቀሊለ አነጋገር የሚሇው አይ ሲ ሲ በሺርን፤ ኬንያታን፤ ሩቶን በነጸጻ መሌቀቅ ያሇበት ካሇፈው ጥፋታቸው በመማር
ስህተታቸውን ተረዴተዋሌ ነው፤ ይህ አባባሌ፡- አንዴ የወንጀሌ ተጠርጣሪ ከክስ ነጻ መሆን ያሇበትያሇፈውን ሃጢአቱን ሁለ ተረዴቶ
በመተው፤ እራሱን በማስተካከሌ ተሃዴሶ አዴረጓሌና፤ ተሇውጦ መጾም መጸሇይ፤ሇተቸገሩ መቸር፤ ቤተእግዚአብሄርን፤መስጊዴን፤
ሲናጎግን፤ የጸልት ቤትን በማክበር መሳሇም ጀምሮ መስረቅ ማጭበርበርን መግዯሌን ስሇተወ ምህረት ሉሰጠው ይገባሌ ነው፡:
የሚያስገርም አስተያየት ነው!
ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን
እውነት ነው ይቀሌዲለ እስካሁን በግፍ የጨረሱትና ያስጨረሱት ህዘብ ዯም የውሻ ዯም ነው፣ ፍትህ ሉያየውአይገባም ይለናሌ ፡፡
የኬንያና የሱዲን አምባገነኖችን ነጻ ሇማዴረግ ሲባሌ እስካሁን የተፈጸመው ሊይጠየቅ እንስማማ ቢለ አይዯንቅም አምባገነኖች ራስ
ወዲድች ናቸውና፡፡ ዕርቅ ማሇት እነሱ ያጠፉት ጥፋት እንዲይነሳ ማዴረግ ብቻ ነው፣ያሇዚያ ሰሊም ሉኖር አይችሌም፡፤ ይህ ተራ አባባሌ
ከትዝብት ውጭ አይ ሲ ሲን ሇማስፈራራት የሚፈይዯው ነገር አይኖርም፡፡በአህጉሩ ውጣ ውረዴ በበዛበት ግጭት ውስጥ ፍትህንና
ይቅር ሇእግዚአብሔርን ማመዛዘን ያስፈሌጋሌ ይሊሌ እራሱን ብቻ አዋቂ በማዴረግ አዴሃኖም ሲናገር:: በዚህ አባባሌ ውስጥ የሚያስገርም
ምጸታዊ አነጋገር አሇ፡፡
የሃይሇማርያምና የቴዎዴሮስ አዴሃኖም ባሇራዕይ እና ኢትዮጵያን ሇአሇፉት አሰርት ዓመታት የገዛው የገዢው ፓርቲ ዋና መሃንዱስ፤
በሞት የተሇየው መሇስ ዜናዊ ሃብቱን በማካባት የበሇጸገው ሇፍትሕና ሇይቅር ሇእግዚአብሔር በሌቡ ቦታ በማጣቱ ሇአነስተኛ
ይቅርባይነት ጨርሶ ፍሊጎትና ፈቃዯኝነት የላሇው ነበር፡፡ ይሄው ባሇራዕይ ገዢ በኢትዮጵያ የተካሄዯውን የ2005 ፓርሊማ ምርጫ
አስመሌክቶ በባድ እጃቸው የዴምጽ መከበርን የምርጫን ሰሊማዊና ፍትሃዊነት ሇማረጋገጥ ሰሊማዊ ሰሌፍ የወጡትን ግዴያ በማዘዝ 193
ዜጎች ሇሞት ሲዲረጉ 763 ዯግሞ በጥይት ቆስሇዋሌ:: ፍትህን ከይቅር ሇእግዚአብሔርን ጋር የሚያመዛዝንበት መንገደ በርካታ
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን የሲቪክ ማህበራት አባሊትን፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፤ጋዜጠኞችን አንዲች ማስረጃ በላሇውና
በጀብዯኝነት በተሞሊ የሃገር ማጥፋት ክስ ሇእስር መዲረግ ነው፡፡ ይሄው ባሇራዕይ እየተባሇ ከበሮ የሚዯሇቅሇት በራሱ ምስሌ በቀረጸው
የካንጋሮ (የዝንጀሮ ችልት) በማቅረብ ፍርዴ አዞባቸው በኋሊ ዯግሞ ተንበርክካችሁ ይቅርታ ጠይቁ በማሇት ሇምህረት ዋጋ ክፈለ ያሇ
እኩይ ባሕሪ የተሊበሰ ነበር፡፡ አሁን እንግዱህ ቴዎዴሮስ አዴሃኖምና ሃይሇማርያም ዯሳሇኝ የሚለት የነዚህ ንጹሃን ዜጎችዯምና
በዲርፉርም የፈሰሰው የንጹሃን ዜጎች ዯም በኬንያም በቅዴመ ምርጫው የዯረሰው ግዴያና ግፍ ሁለ ተረስቶ በሞተ ፋይሌ ይዘጋ ነው፡፡
አአምሮ ያሇው ሰው አንዯዚህ ይናገራሌ?!
አንዯ ሃእሇማርያም አስተያየት እንዳት ነው አይ ሲ ሲ አፍሪካን ነጥል ኢሊማ ያዯረገው? አይ ሲ ሲ ኢሊማ ያዯረገው የሰብአዊ መብት
በሚዯፈጥጡ አምባገነኖች ሊይ ነው፡፡ እነዚህ ዯግሞ በገፍ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው፡፡ ስሇዚህ 99 በመቶ ከአፍሪካ ሆነ የሚባሇው
ከመብት ረገጣው ጋር በቀጥታ የተያያዘ ስሇሆነ ይህም አባባሌ ውሀ የሚቋጥር አይሆንም፡፡የመቶኛ ዴርሻው ፍትሀዊ እንዱሆን በማሇት
የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ ካናዲ፣ አውስትራሉያ፣ ወዘተ መሪዎች በግዴ ወንጀሇኛ ተብሇውምንም ጥፋት ሳይሰሩ መያዝ አሇባቸው እንዳ?
ሰብአዊ መብት ረገጣው እስከቀጠሇ ዴረስ 99 በመቶው አይዯሇም በአፍሪካ አህጉር በኢትዮጵያ ብቻም የማይሆንበት ሁኔታ የሇም፡፡
ዴርጅቱ አፍሪካንና አፍሪካውያንን ሇፖሇቲካ ኢሊማ ያዯረገ ነው ሇሚሇው አለባሌታ ቅንጣት ያህሌ ማሳመኛ እንኳ ሉያቀርቡ
አይችለም፡፡ ምን ሇማዴረግ ነው የፖሇቲካ ኢሊማ ያዯረገው? ማንን? ሇምን? መቸ? እና እንዳት ሇሚለ ጥያቄዎች መሌስም ሆነ
ማስረጃ የሊቸውም፡፡ ስሇዚህ ይህም አባባሌ ተራ አለባሌታ ሆኖ ይቀራሌ፡፡ሃይሇማርያምና አዴሃኖም ሆን ብሇው ማገናዘብ ያሌፈሇጉት
እውነታ፤ (አስተዋይነት የጎዯሊቸው) በአፍሪካ ውስጥስሩን የሰዯዯው በቅዴመ ምርጫ ወቅት በተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ሊይ
በሚዯረግ ተጽእኖ፤ የምርጫ መጭበርበር፤በመጨረሻውም ስሌጣን ዙፋን ሊይ የተኮፈሱት ጉሌበተኞች ሇሽንፈት ሲዲረጉ የምርጫውን
ውጤት አንቀበሌም የማሇታቸውን ሃቅ ነው፡፡ በማያጠራጥር መሌኩ በስሌጣን ሊይ ያለ የአፍሪካ ገዢዎች በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ
ማሸነፍ ስሇማይችለ ሁሌ ጊዜ በተቀናቃኝ ፓርቲዎች ሊይ ያሇውን ህግ በማዲቀሌ ውትፍትፍ ሕግ እያወጡ ሇእስራትና ሇሞት
ይዲርጓቸዋሌ፡፡ ይህ ዯግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በ2005፤በኬንያ በ2007፤ በዝምባብዌ በ2008፤ በ2010 በኮት ዱቩዋር፤በ2011
በዳ/ ኮንጎ እና በማሉ በ2012 መፈንቅሇ መንግስቱ ምርጫውን ባዯናቀፈበት ጊዜ በገሃዴ የታየ ነው፡፡
አዎ እርግጥ ነው ያፍሪካ መሪዎች እነርሱ በህግ የሚጠየቁ ከሆነ እንበጠብጣሇን ሰሊም እርቅ አይኖርም እያለ እያስፈራሩ ነው::
እንዱህም ብል መሪ የሇ፡፡ ራሳቸውን መምራት የማይችለ አምባገነኖች በምን መሌክ ህዝብን ያህሌ ነገር በሰሊምና በፍቅር ይመራለ ተብል ይጠበቃሌ? በምን መሇኪያ ነው እነርሱ የሰሊምና የዕርቅ ጠበቃ ሆነው የአዞ እንባ የሚያነቡት? ጅብ በማያውቁት አገር ሄድ ቆዲ
አንጥፉሌኝ እንዲሇው ነው፡፡ ሇማያውቁሽ ታጠኝ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የወንጀሇኞች ፍርዴ ቤትና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው
ምክር ቤት አዴሎዊ አሰራርነው የሚያራምደት፣ ሇአፍሪካውያን ተጠርጣሪዎች ሲሆን ከባዴና አዴሎዊ የሆነ ቅጣትን የሚሰጡ ሲሆን
ሇላልች ግን የተሻሇ ቅጣትን ነው የሚሰጡት ይሊለ ፡፡ ተራ አለባሌታና ቅጥፈት ካሌሆነ በስተቀር በማስረጃ ቅንጣት ታህሌ መጥቀስ
ይችሊለን? ሇመሆኑ ሇአዴሎዊ አሰራር ቅርብና አዴራጊ ማን ሆነና? ይለሽን በሰማሽ ገበያ ባሌወጣሽ! የተባበሩት መንግስታት
የወንጀሇኞች ፍርዴ ቤት እራሱን ከፍ አዴርጎ የሚያይ ስሇሆነ በዚህ እንዱቀጥሌ እኛ አፍሪካውያን መፍቀዴ የሇብንም፡፡ይኸ ተራ
የበታችነት ስሜት መገሇጫ ነው፡፡ ዴርጅቱ ናቃቸው እንዲይባሌ በወንጀሌ የተዘፈቁትን አምባገነኖች እጁን አጣጥፎ በመቀመጥ ወዯ
ፍትህ አዯባባይ ማምጣት የሇበትም ማሇት ነው? የበታችነትናየበሊይነት ስሜት እንዳት ነው በአምባገነኖቹ የሚገሇጸው? ይህም ተራ
አለባሌታ ካሌሆነ በስተቀር የሚፈይዯው ነገርየሇም፡፡
የሮም ሰምምነት ፈራሚ ሳይሆኑ ነገር ግን ዴርጅቱን ሇመክሰስ ግንባር ቀዯም የሆኑት የእኛዎቹ ገዥዎችያቀረቧቸው 7 ነጥቦች ውሀ
የሚቋጥሩ አይዯለም፡፡ በስሜት የተሞለ ተራ አለባሌታዎች ናቸው፡፡ እንዯሰብሳቢዎች አሊማ ቢሆን ኖሮ ዴርጅቱን እረግጠው ከሮሙ
ስምምነት ሉወጡ ነበር፡፡ ነገር ግን ዴጋፍ ስሊሊገኙ ሳይወደ በግዴ አይ ሲ ሲን እንዱሇማመጡ ጊዜ በይኖባቸዋሌ፡፡ ዓሊማቸው
ሲከሽፍም እኛ ከአይ ሲ ሲ ሇመውጣት አይዯሇም፣ዘረኛና አዴሎዊ መሆኑን ሇማሇጥ ነው የሚሌ የቅጥፈት አለባሌታቸውን ሇማሰማት
ተገዯዋሌ፡፡ ሂዯቱም ሲስሟት ቀርቶ ሲስቧትሆኗሌ፡፡ የሚሰማቸው ቅሬታ ካሇ በማስረጃ አስዯግፈው ማቅረብ ሲገባቸው ዴርጅቱን ጥል
ሇመውጣትና ሇማፍረስ መወጠናቸው ከትዝብት ያሇፈ ፋይዲ አይኖረውም፡፡
የአፍሪካ መሪዎች አፍሪካን የዓሇም አቀፍ ፍርዴ ቤት መቀበርያ አታዴርጓት፡፡ የአፍሪካን ሇምሇም የሳር ምዴር፤በረሃዋ፤ዯኗ፤የአይሲ ሲ
የዲግም ሌዯት ስፍራዋ ይሁን፡፡ አፍሪካን አይ ሲ ሲ ሇዘረኝነት፤ ሇፍትሕ አሌባነት ከተሳሇ ሰይፍነት ወዯየፍትሕ ጋሻ መከታነትና
ትክክሇኛና ሚዛናዊ እንዱሆን አዴርጉ፡፡ አይ ሲ ሲ በኦክቶበር 11-12-13 የአፍሪካ ሃገራት በአንዴነት በመቆማቸው ጠንክሮ ሚዛናዊትክክሇኛና ሚዛናዊ እንዱሆን አዴርጉ፡፡ አይ ሲ ሲ በኦክቶበር 11-12-13 የአፍሪካ ሃገራት በአንዴነት በመቆማቸው ጠንክሮ ሚዛናዊ
ሆኖ በእጅጉ የበረታና ጉሌበታም በመሆኑ አታሞው ይመታ፤ መሇከትም ይነፋ!!
እናንት የአፍሪካ መሪዎች፡ ትክክሇኛውን ተግባር ከውኑ፤‹‹ ካሇያ እግዚአብሔር እና ታሪክ የዛሬውን ውሳኔያችሁን ሲያስታውሱት
ይኖራለ››የአፍሪካ አንዴነት የሮምን ስምምነት እንዱቀበሌ እንጂ እንዲይፍቀው እማጸነዋሇሁ፡፡ በተመሰቃቀሇችው አፍሪካ ነገ፤
በሚቀጥሇው ወር፤ አሇያም በሚቀጥሇው ዓመት ማን ታዲኝ ማን አዲኝ እንዯሆነ አይታወቅም፡፡ ዛሬ በስሌጣን ሊይ ሆኖ የሚያዴነው ነገ
ከስሌጣን ወርድ ተዋርድ ታዲኝ ሉሆን ይችሊሌ፡፡ አይ ሲ ሲ በላሇበት የዛሬዎቹን አዲኞች ከስሌጣን ሲወርደና ሲታዯኑ ማን
ይቆምሊቸዋሌ?
በመጨረሻም በ1935 ኢጣሌያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ ቀ ኃ ሥሊሴ ሇዓሇማ ማሕበሩ አቤቱታ ባሰሙበት ጊዜ የሉግ ኦፍ ኔሽን
ሇአንዱት ዯካማ አባሌ ሃገር ዋስትናና ዴጋፍ ሇመስጠት አሌቻሇም ነበር፡፡ ንጉሡ በዚያን ጊዜ ትዝብታዊ ማስገንዘቢያ አሰምተው ነበር::
እኔም ያንን በከፊሌ ሇአፍሪካ አንዴነት እንዯታሪክ ትምህርትነቱ አመሳስዬ አቀርባሇሁ፡ ‹‹ከእግዚአብሔር መንግስት ውጪ በዚህ ምዴር
ሊይ ማንም ሕዝብ ከማንም የሚበሌጥ አይዯሇም፡፡ ሃያሊን መንግስታት ዯካማዎቹን በሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሌ፤ በጦር ወንጀሌ፤
ሉያጠቁ በሚነሱበት ጊዜ ጉዲትየሚፈጸምባቸው ዯካማ ሃገራት አቤቱታቸውን የዓሇም አቀፉ ፍርዴ ቤት ሚዛናዊና በሕጉ መሰረት ፍትሕ
እንዱሰጥ ይጠይቃለ፡፡የሮምን ስምምነት የምትፍቁት ከሆነ እግዚአብሔርና ታሪክ ፍርዲችሁን ሇዘሌዓሇም ይታዘቡታሌ!
ስሇዚህም በኦክቶበር 11-12-13, 2013 ሇዓሇም አቀፉ ፍርዴ ቤት በምስከረነት ተጠሪ ሆኜ እማኝነት ቆሜያሇሁ! 

No comments: