Saturday, March 1, 2014

Feb 28 2014 የኬንያ ፖሊስ 35 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ማሰሩን አስታወቀ


ኢትዮጵያውያኑ የታሰሩት በኬንያዋ የአይሲዋሉ ጠረፋማ ከተማ ሲሆን ወደ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ሃሳብ እንደነበራቸውም ተጠቁሟል፡፡ የአይሲዋሎ የፖሊስ ሃላፊ ኔልሰን አኪጎ እንዳሉት ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በአንድ ግልሰብ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቻ እንደሆነ እና ሁሉም ምንም አይነት ህጋው ሰነድ እንዳልያዙ የገለጹ ሲሆን የቤቱ ባለቤቶች በፖሊስ ከመያዛቸው በፊት ማምለጣቸውንም ጠቁመዋል፡፡
እንደ ሃላፊው ገለጻ ከሆነ ስደተኞቹ ሊያዙ የቻሉት የአካበቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ በማድረጋቸው እና ፖሊስም በአካባቢው የሚስተዋለውን የህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ተጨማሪ ሃይል በማሰማራቱ ነው ብለዋል፡፡
አካባቢው ከፍተኛ የህገወጥ የሰውዎች ዝውውር የሚካሄድበት መሆኑን የጠቀሱት የፖሊስ ሃላፊው በአካባቢው የሚገኙ ባለሃብቶች እና የቢዝነስ ሰዎች ለዚሁ ተግባር ድጋፍ እና ከለላ በመስጠታቸው ለችግሩን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት አዳጋች እንዳደረገው ገልጸዋል፡፡ የፖሊስ ሃላፊው ቀጣይ የኢትዮጵያውያኑ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ያለው ነገር የለም፡፡ sourse

The greatest WordPress.com site in all the land!

No comments: