Saturday, August 16, 2014

በመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ያልሰለጠኑ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ መግባት ሊከለከሉ ነው


ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስቴር ከ360 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመንግሥትን ፖሊሲና
ስትራቴጂን እንዲሰለጥኑ አስገዳጅ መመሪያ ያወጣ ሲሆን በሥልጠናው ላይ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ያልያዘ ተማሪ በዩኒቨርሲቲዎቹ ትምህርቱን
መቀጠል እንደማይችል በግልጽ አስጠንቅቋል፡፡ የትምህርትሚኒስትሩአቶሺፈራውሽጉጤሰሞኑንለጋዜጠኞችእንደገለጹትበመንግሥትፖሊሲዎችና
ስትራቴጂዎችላይ ከ250ሺህበላይነባርየዩኒቨርሲቲተማሪዎችእናከ116 ሺህበላይአዳዲስተማሪዎችለተከታታይ 15 ቀናት አበልበመክፈልባሉበት
አካባቢበፕላዝማሥልጠናእንደሚሰጥአስታውቀዋል፡፡ የሥልጠናውየመጀመሪያዙርከሳምንት በኃላእንደሚጀምርያስታወቁትሚኒስትሩሁለተኛው ዙር
በመስከረምወር 2007 ዓ.ምተሰጥቶለማጠናቀቅመታሰቡን ተናግረዋል፡፡ ሥልጠናውንየሚሰጡትከፍተኛየመንግሥትባለስልጣናትመሆናቸውን
የሥልጠናውዝርዝርእናየሚፈጀውወጪምንያህል እንደሆነተጠይቀውከመናገርተቆጥበዋል፡፡ሆኖምሌሎችምንጮችበሥልጠናውከተካተቱት ርዕሰ
ጉዳዮችመካከል ስለሃይማኖትአክራሪነት፣ስለሽብርተኝነት፣ስለልማታዊመንግሥትጉዳዮችእንደሚገኙበትጠቅሰዋል፡፡ ይህሥልጠና ኢህአዴግ በመንግሥት
ወጪለቀጣዩምርጫድጋፍለማግኘትእንዲሁም ነባር አባላቱን በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመተካት ለዘረጋው መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ ነው በሚል አስተያየቶች
ይሰጣሉ። ምንጮች እንደሚሉት ለፓርቲው ስራ ገንዘብ እንዲወጣ የሚደረገው ከመንግስት ካዝና ነው። በተመሳሳይ ዜና ደግሞ ባለፈውሰኞየተጀመረው
ለፌደራልዳኞች፣አቃቤያነ ህጎች፣ የፖሊስናየደህንነትሃላፊዎችየሚሰጠው የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ስልጣና እንደቀጠለ ነው። በተወካዮች ምክር ቤት
እየተካሄደ ባለው ስልጣና  ተሳታፊዎቹበአይነትናበይዘትየተለያዩጥያቄዎችንአንስተዋል። አንድ ተሳታፊ “የዚህዓይነትስልጠናበዚህወቅትበተለይለኛለምንኣስፈለገ?የፍትሕኣካላትበተለይዳኞችከፖለቲካነጻናቸውበሚባልባትሃገርውስጥበተለይየስልጠናማንዋሉየኢሃዴግንአርማመያዙየዳኝነትን ገለልተኝነት
ጥያቄ ውስጥ አያስገም ወይ?” የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ሌላ ተሳታፊ ደግሞ ” ኢሃዴግለ23አመታትየገዛፓርቲ ሆኖሳለለ10ዓመታትእድገትአመጣሁ ማለቱ
ድክመቱንከመግለጽ ይልቅ ስለ እድገትናስልጣኔብቻማዉራቱምንማለትነው? ” ሲሉ ጠይቀዋል። ከታሪክ ጋር በተያያዘ በተነሳው ገለጻ ላይ ደግሞ አንድ ጠያቂ
” አጼሚኒሊክወራሪነውወይስሃገር አቅኚወይምተስፋፊ?በሚኒሊክዘመንየነበረው የመደብጭቆናነው ወይስየብሄርጭቆና ?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ቋንቋን
በተመለከተም ” ኣንድኢትዮጵያንለመፍጠር አንድቋንቋአያስፈልግምወይ?” የሚሉእናሌሎችተዛማጅ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳለተነሱት
ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን፣ አጼ ሚኒሊክን በተመለከተ በሰጡት መልስ  አጼ ሚኒሊክ ወራሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።  በሚኒሊክወቅትየነበርው ጭቆና
ሁለትገጽታነበረውያሉት አባ ዱላ “በአማራክልልየመደብጭቆና ፣በኦሮሚያናበደቡብክልሎች ደግሞ የብሄርጭቆና  ነበር ” ብለዋል። ስርዓቱየሚከተለዉን
ኣይዶሎጂበሚመለከት በሰጡት ገለጻ ደግሞ “ኢህአዴግ የታይዋንናየህንድን ልማታዊመንግስታትርእዮት አለምወይምአስተሳሰብእንደሚከተሉነገርግን የኢህአዴግ
ርእዮት አለም  እንደነሱልማትንበግድየሚጭን መንግስትሳይሆን፣ልማታዊና ዲሞክራሲያዊነው” ብለዋል።ተሰብሳቢዎቹም ” የነታይዋንአይነትልማትንበግድ
የሚጭንመንግስትእንዴትዲሞክራሲያዊይሆናል?” የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ኢህአዴግ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችን ፣ የመንግስት ሰራተኞችን፣
የህዝብ ተወካይ የሚባሉትንና የግንባሩን ካድሬዎች ሰብስቦ በወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ እያነጋገረ ነው።       sourse esate radio

No comments: