Sunday, August 10, 2014

በሐሰት መንግስታዊ ማጭበርበሮች ሳንታለል በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎችን እናረጋግጥ !!! ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)



በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ በትክክለኛው መንገድ የማያስቀምጡ የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ዘገባዎችን በመስራት እና እውነትን ለመሸፋፈን በመትጋት የሕዝቦችን የማወቅ መብት ያለርሕራሄ እየተጋፉ ይገኛል። ይህ በወያኔ የፕሮፓጋንዳ አካላት የሚፈጸም ማጭበርበር እና ማደናገር የገዢውን ፓርቲ ውስጣዊ ዝርክርክነት በይፋ ያሳብቃል።ያለለውን እንዳለ ድሮ ተግንብቶ የታደሰውን እንደ አዲስ እንደተገነባ ፤ ያልተሰራውን እንደተሰራ ሕዝቡ የማያገኘውን አገልግሎት እንደሚያገኝ ወዘተ በማድረግ በሁለት እና ሶስት እጥፍ በማባዛት በመቶኛ በማስላት በመደመር በማባዛት ያሌለውን ምስል በመፍጠር ሕዝቡን እያደናበሩ ይገኛሉ።
በአለም ላይ ካሉ መንግስታት በተለየ ሁኔታ ዜጎቹን እያጭበረበረ ወደ ድህነት አዘቅት እየከተተ ያለ መንግስታዊ አስተዳደር ነኝ የሚል ቢኖር ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው። የወያኔ የማይሳኩ እና የሚያደሐዩ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ፖሊሲዎች መነሻቸው የተሳሳቱ ፕሮፓጋንዳዎች ናቸው። ማንኛውንም ፖሊሲ ይሁን አዋጅ መመሪያ ይሁን ደንብ ወያኔ ሲያወጣ በተቆጣጠራቸው ሚዲያዎቹ እያጋነነ የሕዝብን ልብ ለመስቀል በመሞከር እደርስበታለው ያለው ግብ ምንግዜም እየተኮላሸ ተጨባጩን ሁኔታ ባለማገናዘብ እየካደ ስለሚጓዝ የሃገር ኢኮኖሚ የጨው ክምር በመሆኑ እየተናደበት ይገኛል።
ሕዝቡ ትክክለኛ አስተዳዳሪ ባለማግኘቱ ምክንያት እየተንገላታ በየቦታው ምሬት በበዛበት በአሁኑ ሰአት ተገቢውን አገልግሎት እንዳገኘ በማድረግ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ለማሳሳት እየተሞከር ሲኦን በቀረቡ መዝገቦች ላይ ውሳኔ መስጠት አቅቶት ወይም በቸልተኝነት አልወስንም ብሎ የሚኮፈስ ቢሮክራሲ ዜጎችን ሲያስለቅስ በአደባባይ እየታየ መፍትሔ እየተገኘ ነው የሚል ማደናገሪያ ሲቀርብ ያሳዝናል፡፡ ያሳፍራል፡፡በፍትሕ ሥርዓቱ አካባቢም ሲታይ እየወጡ ያሉ መግለጫዎችና ሪፖርቶች የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ፍትሕ ዘገየብን፣ ፍትሕ ተነፈግን የሚሉ በርካታ ዜጎች ባሉበት አገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓቱ ተደራሽነት ወደር የለውም ዓይነት ሪፖርቶች ይቀርባሉ፡፡ ሕዝቡ በየፍርድ ቤቱ በተጓደለ ወይም በተነፈገ ፍትሕ ምክንያት ከላይ ታች ሲቅበዘበዝ እየታየ የማይመስል ነገር ይነገራል፡፡ በዚህ መስክ ያለው ማደናገር ራስ ያሳምማል፡፡
በኑሮ ውድነት በትራንስፖርት በውኃ በኤሌክትሪክና በስልክ አገልግሎቶች አለመሟላት እና መቆራረጥ ምክንያት ሥራውና ኑሮው አሳር እያየበት ያለው ሕዝብ የአገልግሎቱ ተደራሽነት በዚህን ያህል በመቶ አደገ ወይም ደረሰ ሲባል ቀልድ የተያዘ ይመስለዋል፡፡ ለሳምንታት ውኃ አጥቶ የሚንከራተት ሕዝብ የውኃ ተደራሽነት ከዘጠና በመቶ በላይ ሆኗል ተብሎ ሲለፈፍበት እንዴት ይቀበላል? በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ምክንያት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ማምረት እያቃተውና ሕዝቡ በጨለማ ሲሰቃይ ተደራሽነቱ ይህን ያህል ደርሷል ሲባል ማን ያምናል? በሌሎች ዘርፎችም ተመሳሳይ ማደናገሪያዎች ሞልተዋል፡፡ከመሃል አገር እና ከተለያዩ ክፍለሃገሮች ገበያዎች የተገኙ ተብለው የሚቀርቡ የእህል ዋጋዎች መጋጨት የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ጤፍ፣ በርበሬ፣ ጥራጥሬና የተለያዩ የግብርና ምርቶች ዋጋ በወያኔ መገናኛ ብዙኃኑ ሲተነተን፣ በፍፁም ገበያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያሳይም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ማደናገሪያ ማንን እንደሚጠቅም አይገባንም፡፡ ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል።
ስለዚህ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አንዱ ለሌላው መረጃዎችን በማስተላለፍ ወያኔ እና ሚዲያዎቹ የሚጠቀሙበትን የማደናበሪያ ስልት በማጋለጥ እና ሊደናበር የሚችለውን የዋሁን ኢትዮጵያዊ በማስረዳት የዜግነት ግዲታችንን እየተወጣን በጋራ በመታገል ይህንን ውሸታም እና አጭበርባሪ አደናባሪ ስርአት ልናስወግደው እና ለመጪው ትውልድ እውነትን የተሞላች አገር የማስረከብ ሃላፊነት እንዳለብን ለማሳሰብ እወዳለሁ። በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎቻችንን እናረጋግጣለን!!1 #ምንሊክሳልሳዊ
sourse abugida

No comments: