Monday, September 15, 2014

የተከፋፈሉት የሶማሊ ክልል ስራ አስፈጻሚ አባላት አንዱ ሌላውን ከስልጣን ማገዳቸውን አስታወቁ


መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት የሶማሊ ክልል መሪዎች፣ የደህንነት ሃላፊዎችና በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በተገኙበት በተደረገው ግምገማ በፕሬዚዳንቱ
አብዲ ሙሃመድ ላይ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ከቀረቡ በሁዋላ ፣ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ በሚፈልጉት  የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና በክልሉ የመከላከያ ሹም ጄኔራል አብርሃ መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል።
ውሳኔ ለመስጠት የተቸገሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ ግምገማው እንደተጠናቀቀ፣ ሁሉም የክልሉ ባለስልጣኖች ወደ መጡበት እንዲመለሱ አድርገዋል።
የክልሉ የስራ አስፈጻሚ አባላት ወደ ጅጅጋ ከተመለሱ በሁዋላ አንዱ ሌላውን ለማጥቃት ሃይል ሲያሰባስብ ቆይቷል። የክልሉ ፕሬዚዳንት የአገር ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ ከስልጣን የሚነሱ ከሆነ እርሳቸው የሚመሩትን ልዩ ሚሊሺያ
ለጥቃት እንደሚያሰማሩት በመግለጽ ሽማግሌዎቹ ከጎናቸው እንዲቆሙ የማስፋራሪያ ተማጽኖ ቢያደርጉም የአገር ሽማግሌዎች ግን በጉዳዩ ጣልቃ እንደማይገቡ ለአቶ አብዲ ገልጸውላቸዋል።
ከ 11 የስራ አስፈጻሚ አባላት መካከል 7ቱ በአቶ አብዲ ላይ የተነሱ ሲሆን ባለፈው ሳምንት የምክር ቤት አባላትን ድጋፍ ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ፣ የልዩ ሚሊሺያ አባላት ባደረሱባቸው ማስፈራራት ወደ ድሬዳዋ ለመሰደድ ተገደዋል።
የምክር ቤት አባላቱን መሰደድ አጋጣሚ በመጠቀም አቶ አብዲ፣ 7ቱ የስራ አስፈጻሚ አባላት ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ያስታወቁ ሲሆን፣ 7ቱ የስራ አስፈጻሚ አባላትና አንዳንድ የምክር ቤት አባላት አቶ አብዲን ከፕሬዚዳንትነት
ማንሳታቸውን የሚያመለክት ደብዳቤ በትነዋል።
የፌደራሉ መንግስት ለየትኛው ወገን እውቅና እንደሚሰጥ ባይታወቅም፣ በኦጋዴን ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀል አቶ አብዲን ተጠያቂ ለማድረግና ማእከላዊውን መንግስት ነጻ ለማድረግ ከስልጣን ሊያነሳቸው
ይችላል በማለት አንዳንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለኢሳት ተናግረዋል።
አቶ አብዲ ልዩ ሚሊሺያው በክልሉ በተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ክልሉን ነጻ እንደሚያደርጉ በመዛት በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚጠቀሙበት ዘዴም፣ ረጅም ርቀት እንደማይቀወዳቸው እነዚሁ
አስተያየት ሰጪዎች ይ                 sourse  esat radio

No comments: