Sunday, October 19, 2014

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአንድ የምርት ዘመን 50 ሚሊዮን ኩንታል ልዩነት የታየበት መረጃ ሰጡ


ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተቃዋሚ የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ኢትዮጵያ በምግብ ራሱዋን ችላለች በሚል  በተደጋጋሚ ቢነገርም አሁንም ስንዴ ከውጭ እያስገባን ነው በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ጠ/ሚንስትሩ “በምግብ ራሳችንን መቻላችንን”
አለማቀፍ ተቋማት ሳይቀር ያረጋገጡት መሆኑን በመግለጽ፣ ኢትዮጵያ በአለፈው አመት 300 ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት ማምረት መቻሉዋን ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ የግንቦት20 በአል በሚከበርበት ወቅት ጠ/ሚኒስትሩ ባቀረቡት ንግግር ኢትዮጵያ በተጠቀሰው አመት 250 ሚሊዮን ኩንታል ማምረቷን ተናግረዋል
በአንድ የምርት ዘመን አንድ ጊዜ 250 ሌላ ጊዜ 300 ሚሊዮን ኩንታል  ምርት ተመርቷል በሚል የሚቀርበው ሪፖርት መንግስት ለህዝብ የሚያቀርበውን ሪፖርት ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። አትዮጵያ 50 ሚሊዮን ኩንታል ተጨማሪ ምርት ለማምረት በትንሹ ከ 5 አመት
ያላነሰ ጊዜ የሚወስድባት ቢሆንም፣ ጠ/ሚኒስትሩ በ3 ወር ውስጥ ተጨማሪ  50 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደተመረተ አድርገው ለፓርላማው ያቀረቡት ሪፖርት አጠቃላይ የቀረበውን ሪፖርት ባህሪ የሚያሳይ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።
ኢትዮጵያ ረሃብን በማጥፋት የሚሊኒየም የልማት ግቦችን አሳክታለች በማለት ጠ/ሚንስትሩ ያቀረቡት ሪፖርትም ፍጹም ሀሰት መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ድርጅት ያወጣውን ሪፖርት በመጥቀስ ዘግቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት 28 በመቶ
ኢትዮጵያውያውያን አሁንም በአስከፊ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑን ያሳያል።ESAT Amharic

No comments: