Thursday, October 23, 2014

በኦሮሚያ ና በአማራ ከልሎች የግሪሳ ወፍ መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የግሪሳ ወፍ በሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዛሬ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት በፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ከበደ ላቀው እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል ዝዋይና መቄ አካባቢዎች 8 ሚሊዮን ሚጠጋ የግሪሳ ወፍ ተከስቷል፡፡ በአማራ ክልልም ሰሜን ሸዋ ቀወት እንዲሁም ኤፍራታና ግድም ወረዳዎች 1.5 ሚሊዮን የሚሆን የግሪሳ
ወፍ ተከስቷል ብለዋል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ባደረገው የመከላከል ስራ ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ የግሪሳ ወፍ መከላከል እንደተቻለ ባለሙያው ገልፀዋል፡፡ እስካሁንም ከአካባቢው በተገኝ መረጃ መሰረት ወፉ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱ የተገለፀ ሲሆን ፤ መንግስት እርመጃ
እንዲወሰድ ጥረት አላደረገም ሲሉ በመውቀስ ላይ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት በአፋር እና አማራ ክልል ወፉ ተከስቶ በደረሰ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡ ስለጉዳዩ ያነጋገረናቸው የክልሉ ግብርና ቢሮ አርሶ አደሩ በራሱ ጥረት ወፉን ከመለከላከል የዘለለ በመንግስት የሚደረግ ድጋፍ የለም ብለዋል፡፡      sourse esate

No comments: