Tuesday, April 15, 2014

በፈረንሳይ ፓሪስ ከጎዳና ተዳዳሪነት ያወጡት ኢትዮጵያዊት እናት እና ልጅን ገድሎ የተሰወረው ግለሰብ ተያዘ


by admin
ማርች 6 ቀን 2014 ዓ.ም በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ላይ “በፓሪስ ኢትዮጵያዊው ከጎዳና ተዳዳሪነት ያወጡትን እናትና ልጅ ገድሎ ተሰወረ!” በሚል ዜና አስነብበናችሁ ነበር።
የዘ-ሐበሻ የአውሮፓ አካባቢ ወኪል ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ በወቅቱ ይህን ዜና ሲዘግበው “እናትና ህጻን ልጅዋን ገድሎ የተሰወረው ሰውዬ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በፈረንሳይ ፓሪስ ክርተማ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ነበር:: ሟች ወ/ሮ ክውን ገዳሙ ትባላለች:: ከቤትዋ ወደ ስራ ቦታ ሲመላለሱ ተጠርጣሪውን የዩታል:: በጎዳናው የተጎሳቆለውን ሰው(ጉዳዩ በህግ ስለተያዘ ስሙን እዚህ ላይ አንጠቅሰውም) ስለሚያሳዝናቸው ባለፉ ባገደሙ ቁጥር እጃቸውን ይዘረጉለት ነበር::
ከግዜ በኋላ ከክረምቱ ብርድ እንዲገላገል ሲሉ ይህንን የጎዳና ተዳዳሪ ለግዜው በቤታቸው አስጠጉት:: የአቅማቸውን እየረዱት አብረው ለወራት ኖሩ:: ባለፈው ሳምንት (ሜይ መጀመሪያ ላይ) አንድ አስደንጋጭ ክስተት በቤተሰቡ ውስጥ ተፈጸመ:: በችግሩ ያስጠጉት ሰው ከተኙበት በጭካኔ ገድሏቸው አመለጠ::
ወ/ሮ ክውን ገዳሙ የሶስት ልጆች እናት ሲሆኑ በፈረንሳይ ፓሪስ ለረጅም ግዜ ኖረዋል:: የሶስት ልጆች እናትም ናቸው:: ያለአባት ከሚያሳድጓቸውን ሶስት ልጆች ውስጥ አንደኛዋና የሁሉም ታናሽ ከሆነችው ጋር ላይመለሱ ይህችን አለም ተሰናበቱ::
ገዳዩ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በጩቤ ሰነጣትቆ ነው እናትና ልጅን ለህልፈት የዳረገው- እንደ ፈረንሳይ የዜና ምንጭ:: ባጎረሱት እጅ ተነከሱ:: ደግ ባደረጉ ምላሹ ግድያ ሆነ: ለዚያውም አረመኔያዊ ግድያ::
ነብሰ ገዳዩ ለግዜው ተሰውሯል:: የፈረንሳይ ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመሆን ጉዳዩን በጥብቅ ይዞታል:: እኛም እየተከታተልን ጉዳዩ ምን እንደደረሰ እናቀርብላችኋላን::” ይል ነበር በወቅቱ ያቀረብነው ዜና።
ዛሬ ከፈረንሳይ በደረን መረጃ መሠረት ኢትዮጵያዊቷን እናት ልጅ የገደለው ወጣት በፈረንሳይ ማርሴይ ከተማ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ቀጣዩን ሁኔታ መረጃዎችን አሰባስበን ተከታትለን እንዘግባለን።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

No comments: