Wednesday, May 28, 2014

ሰበር ዜና:- ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ መንግስት አሁንም ሌላ ጋዜጠኛ አስሯል


10413437_388278764646421_549629776073588236_nየኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ላይ የፈፀመውን እስር ተከትሎ የኢቦኒ መፅሔት መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ ጋዜጠኛው በሀገሪቱ ያለው የፕሬስ ነፃነት አፈና ተጠናክሮ በመቀጠሉ እና መንግስት ሊወስደው ያሰበውን እርምጃ በመሸሽ እንደተሰደደ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ እና በሌሎች የኢህአዴግ ደጋፊ ናቸው በሚባሉ እንደነ አይጋ ፎረም እና ሆርን አፌይርስ የመሳሰሉ ድህረ-ገሮች የተለያዩ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ዞን 9 ብሎገሮች እንዲታሰሩ እና እንደሚታሰሩ ፍንጭ መስጠታቸው ለስደቱ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ከመጪው ምርጫ 2007 ዓ.ም. በፊት የመንግስትን ብልሹ አሰራር እና ኢሰብዓዊ ድርጊት በመኮነን ያጋልጣሉ የተባሉ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች እንደሚታሰሩ በተለያየ ጊዜ የተነገረ ቢሆንም፤ በቅርቡ 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በመንግስት የተወሰደው የጋዜጠኞች እና ብሎገሮች እስር ተከትሎ ሌሎችም ሊታሰሩ እንደሚችሉ በተዘዋዋሪ መንገድ መገለፁን ተከትሎ ከጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ በፊት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እና ፍስሃ ያዜን ጨምሮ አራት ጋዜጠኞች መሰደዳቸው ታውቋል፡፡ ጋዜጠኞቹ ከሀገር ጥለው መሰደዳቸው በስተቀር እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡
10349201_388278847979746_1177373740366465021_nይህ በእንዲህ እንዳለ የእንቁ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከስራው ጋር በተያያዘ በእንቁ መፅሔት በተፃፈ ፅሑፍ ከማዕከላዊ ቃሉን እንዲሰጥ በስልክ በተደረገለት ጥሪ ትናንት ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደስፍራው ቢያቀናም ማረፊያው እዛው ማዕከላዊ እስር ቤት ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ በዋስ ይለቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም እስር ቤቱ ፍርድ ቤት አቅርቦት የዋስ መብት ሳይከበርለት ለተጨማሪ 7 ቀናት እዛው ማዕከላዊ ታስሮ እንዲቆይ ተጠይቆበት በእስር ላይ ይገኛል፡፡
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

No comments: