Thursday, May 22, 2014

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ በድንጋይ ተፈነከተ – ዳዊት ሰለሞን

sourse abugida



የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ አባልና የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ትናንት ለምሳ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲያቀና ማንነታቸውን ባልለያቸው ሰዎች በድንጋይ መፈንከቱ ታውቋል፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 8፡00 እንደደረሰ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ በመቅረብ ምንም ሳያነጋግሩት በድንጋይ ፈንክተውት መሰወራቸውን አቶ ስንታየሁ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ በድንጋይ ከተፈነከተ በኋላ ለደቂቃዎች ራሱን ስቶ የወደቀው አቶ ስንታየሁ በሰዎች እገዛ ህክምና አግኝቶ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡ አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት››የሚለውን ህዝባዊ ንቅናቄ መጀመሩን ተከትሎ አቶ ስንታየሁ ታላቅ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ፓርቲው በመስከረም 19 እና ሚያዚያ 26/2006 አዲስ አበባ ላይ ባደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎች ስንታየሁ እጆቹን በካቴና አስሮ በእስር ቤት የሚገኙትን የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ትኩረት እንዲያገኙ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ በቅርቡ አንድነት ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ስራ ለመስራት ስንታየሁ ከሌሎች የፓርቲው አባላት ጋር ሲንቀሳቀስ በፖሊስ ተይዞ በህገ ወጥ መንገድ ታስሮ መለቀቁም አይዘነጋም፡፡10154555_639499512801653_5969422659507883103_n
10314575_639499562801648_4420314162813658684_n
10337743_639499116135026_2659494737526262861_n
10372064_639499472801657_6139435484836598111_n

No comments: