Friday, August 30, 2013

ህዝብን ማዳመጥ ያልቻለው ራሱን የሚያዳምጠው ወያኔ--ህዝብን የማያዳምጥ ራሱን የሚያዳምጥ የማይደመጥ ይሆናል፡፡

Thursday, August 29, 2013


ህዝብን ማዳመጥ ያልቻለው ራሱን የሚያዳምጠው ወያኔ

ምንሊክ ሳልሳዊ


ስብሰባ ስብሰባ ስብሰባ.....ይቀጥላል ይህ ወያኔያዊ የአውሬ ወለድ በሽታ
 ...ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እናዳምጣቹ በሚል ሰበብ ችግራችሁን ተወያይተን እንፍታ በሚል ሰበብ የተለያዩ ስብሰባዎች የህዝብን ጭንቅላት ለመስረቅ በጀት ለአበል ተመድቦ እበማካሄድ ምንም ፋይዳ ያሌላቸው እና ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል የሚደረጉ ከመሆናቸውም በላይ ወያኔ ግን የሚወስነው ጉዳይ ለህዝብ እንቅፋት የሆነ እና ከስብሰባው እና ከተሰብሳቢ ምልክታ ውጪ የፖለቲካ አጀንዳውን ለማስፈጸም ብቻ ነው::

በስብሰባ ስም የሰበሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተጠሩበት አጀንዳ ውጪ ራሱ ተናግሮ ራሱ እንደፈለገ አውጥቶ እና አውርዶ ራሱ ወስኖ የራሱን ድምጾች እንደገደል ማሚቱ የሚያዳምጠው ወያኔ ምንም አይነት መንግስታዊ እና ህዝባዊ ፋይዳዎችን ሲፈጽም አልታየም::ህዝብን ማዳመጥ አለመቻሉ ህዝብ ጥያቄ ሲያነሳ እንደ ጭራቅ መመልከቱ የመብት ጥያቋ ያለሳ ሁሉ እንደ ጠላት እና እንደ ተቃዋሚ መፈረጁ ወያኔ ህዝብን ለማዳመጥ ጊዜ እንዳሌለው የሚያሳዩ ጉዳዮች ናቸው::ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አውቅልሃለሁ ከተባለው ውጭ ጥያቄ አንስቶ ቢገኝ ህገወጥ ነው:: የፖለቲካ ፓርቲ ሰልፍ ቢጠራ ህዝብ በአደባባይ የአገልግሎት መብቱን ቢጠይቅ በስብሰባ ላይ የተሰማውን ቢተነፍስ  ወዘተ...ህገወጥ ነው::

በአለማችን ላይ አንዱ አንዱን ካዳመጠ የማይፈታ የማይቀረፍ ችግር የለም:: በሰለጠነ ዘመን እኔን ብቻ ስሙኝ ብሎ ድርቅ ያለ አስተሳሰብ ማንጸባረቅ ተቀባይነት የለውም:: ህዝብን ማዳመጥ የቻለ መንግስት ነኝ የሚል ሁሉ ሃገራዊ ስኬቶቹ ጉልህ ናቸው::ህዝብን ማዳመጥ ያልቻለ በጉልበት የሚኖር መንግስት የግእዜ ጀግና ስለሆነ ይወድቃል:: ወያኔም እኔ ብቻ ነኝ ህዝባዊ ሌላው ህገወጥ ነው ቢልም ለህዝብ ችግሮች ግን ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጥ ባለመቻሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች በስፋት እየጨመሩ መተዋል::

በየስብሰባው ገበሬው ነጋዴው መምህሩ ተማሪው ፖለቲከኛው ጋዜጠኛው ....ባጠቃላህ ህዝቡ ብሶቱን አሰምቷል::የህዝብን ችግር እናዳምጣለም በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦ ስብሰባዎች በየፈርጁ ተጠርቷል::ሁሉም ችግሩን ተንፍሷል:: ...መፍትሄ ግን የለም:: የህዝብን ጥያቄ ግን ወያኔ ሊያዳምጥ አልፈቀደም ....ይልቁኑ ለሚዲያ ፍጆታ እና ለፖለቲካ አጀንዳነት ተጠቅሞበታል:: በየስብሰባው አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ተናግረዋል የተባሉ ታፍነዋል ታስረዋል ተሰደዋል ተገድለዋል ከስራ ተባረው ቤተሰባቸው እንዲበተን ተደርገዋል::ታዲያ ህዝብን ማዳመጥ ተብሎ የሚጠሩ ስብሰባዎች ወያኔ ራሱን እያዳመጠ ህዝቡን እየደፈጠጠ ነው::

የህዝብ ጥያቄዎች አለመደመጣቸው ውጤቱ የችግሩን ጥልቀት ስፋት እና እያስከተለ ያለውን ቀውስ ሊታየው ያልቻለው ወያኔ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ህዝቡን ወደባሰ የድህነት አረንቋ እየከተተው ነው:: ይህ ደሞ ወያኔ እንደ መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች አትኩሮት አለመስጠቱ ነው::ሕዝብ ችግሩን የሚናገረው በስብሰባ ብቻ አይደለም፡፡ በየቀበሌው፣ በየክፍለ ከተማው፣ በየከተማ አስተዳደር እርከኖች፣ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በየክልሉ፣ ወዘተ  በማመልከቻ፣ በቃልና በጽሑፍ በየደቂቃውና በየሰኮንዱ አቤት እያለ ነው፡፡ የሰሚ ያለህ እያለ እየጮኸ ነው፡፡ መብቴ ተረገጠ፣ ንብረቴ ተቀማ፣ ጉቦ ካልሰጠህ ችግርህ አይፈታልህም ተባልኩ፣ አድልዎ ተፈጸመብኝ፣ ወዘተ እያለ ነው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ የሚያዳምጠው የሚያዳምተው አላገኘም ካድሬዎች ከህዝብ ጥያቄዎች በፊት  ፖለቲካውን እና ተቃዋሚዎችን ወደ ማሳደድ አዘንብለዋል::

ህግ አለ ህገመንግስት እናስከብራለን የሚለው ወያኔ መጀመሪያ ራሱ ህገ መንግስቱን እና ያወጣውን ህግ ማክበር አለበት::አንድ መንግስት ህዝብን ያዳምጥ ሲባል መለመን ወይንም ምጽዋት መጠየቅ አይደለም:; ህዝብም ማዳመጥ የማንኛውም አመራር ህጋዊ ግዴታ ነው::ህዝቦች ከህግ እና ከመብት አንጻር ተደምጠው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል::መንግሥት ሕዝብን የሚያዳምጠው በሕገ መንግሥቱ ግዳጅነት አይደለም፡፡ የሕዝብ ሰራተኛ ነኝ የሚል ሥልጣን የያዘ ፓርቲና መንግሥት፣ ሕዝብ መረጠኝ የሚል ፓርቲና መንግሥት፣ የሕዝብ ከበሬታና አመኔታ ሊያገኝና ዓላማውን በተግባር ላይ ሊያውል የሚችለው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ የሚቆየው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ህዝብን የማያዳምጥ ራሱን የሚያዳምጥ የማይደመጥ ይሆናል፡፡

No comments: