Wednesday, August 28, 2013

በሙስና ስም የሚደረጉ አፈናዎች ወደ ግሉ ዘርፍ ሊዞሩ ነው::


የጸረ ሙስና አዋጁ በድጋሚ ይደነገጋል:: የጸረ አሸባሪነት ህጉሳ???

በባለስልጣናት እና በወያኔ ድርጅቶች ላይ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን እና ሰነዶችን ያጠፋሉ የተባሉ የሕወሓት ሰዎች በጸረ ሙስና ኮሚሽን አደረጃጀት እና የሰው ሃይል ጭማሪ ሰበብ አስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ለመሰግሰግ ስልተና እየተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል::
የሙስና ቁጥጥሮች ከግሉ ዘርፍ ላይ ከማተኮር ይልቅ በፖእቲካው ዘርፍ ውስጥ የሚያጭበረብሩ ቱባ ባለስልጣናትን ለምን እንደማይጠይቅ ሊገባን ስላልቸለ ቢተነተንልን እንመርጥ ነበር ሆኖም የዚህን ትንታኔ ሃላፊነት መውሰድ የሚችል በኢ ሞራል ያለው ባለስልጣን መጥፋቱ እንዲድበሰበስ ተድበስብሶም እንዲቀበር (እውነት ባይቀበርም)ለማድረግ እየተደረገ ነው::

የፖለቲካ ሹመኞችን በአሸባሪነት ህግ እንዲሁም ጋዜጠኞችን እና የሃይማኖት መሪዎችን ጨምሮ በማፈን ሃገሪቷን ያለሃሳብ ህዝብን ያለ እውቀት ለማደንዘዝ እየሰራ ያለው የወያኔው ቡድናዊ አምባገነን አገዛዝ የራሱን ሰዎች የሚያጠምድበትን የሙስና አዋጅ አውጥቶ የፈለገውን ድባቅ ከመታ በኋላ በቱባዎቹ ባለስልጣናቱ ላይ ጥያቄ ሲነሳ የህዝቡን ጭንቅላት ለመስረቅ (በሙከራ ላይ)የሙስና ኮሚሽኑን አይኖች ወደ ግሉ ዘርፍ እንዲያዞር በግድ በመጠምዘዝ የሙስና አዋጁን በድጋሚ ለመደንገግ ተገዷል::

የጸረ ሙስና አዋጁ በድጋሚ የተደነገገው በግሉ ዘርፍ ያሉትን እና በመልካም አስተዳደር እና የስራ አመራ የወያኔን የንግድ ድርጅቶች የሚመሩትን የግሉን ዘርፍ ባለስልጣናት በሃሰት ክስ በሙስና ስም በመተብተብ ዘርፉን ለማዳከም የተደረገ ደባ ነው"
አዲስ ተብሎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚጸድቀው አዋጅ በህዝብ ገንዘብ የሚተዳደሩ ህዝባዊ ድርጅቶች እና ማህበራትን ተብለው የሚጠሩ አካላትን የወያኔው ጁንታ ለራሱ በመቆጣጠር በእጁ ያልገባለትን የሃገር እና የህዝብ ገንዘቦችን እና ንብረቶችን ለመዝረፍ እንዲያመቸውእና ፖለቲካውን አላስገባ ፖለቲከኞችን አላስበላ ያሉ የድርጅቶችን እና የማህበራትን አስተዳደሮች እና አመራሮች ለመጥለፍ የተሸረበ ሴራ ነው::

እንዲሁም የአክሲዮን ማህበራትን ባንኮችን የኢንሹራንስ ካምፓኒዎችን አዳክሞ ከገባያ ውጪ በማድረግ የስራ አመራሮችን ወደ ወህኒ በሃሰን የሙስና ወንጀል በመክተት የሕወሓት መራች የንግድ ድርጅቶች ገበያውን እንዲቆጣጠሩት እንዲሁም ከተቃዋሚዎች ጋር በቅርበት አሉ የሚባሉ የግሉ ዘርፍ የተማሩ ባለሙያዎችን ለማፈን ይረዳ ዘንድ የጸረ ሙስና ህጉ በድጋሚ ፖለቲካዊ መልኩን በማጠናከር እንደሚጸድቅ ይጠበቃል::ከዚህ ቀደም አዋሽ ባንክን ለማዳከም ተንካራ ስራ አስኪያጅ የሆኑትን አቶ ፀሃይን በፈጠራ ክስ ለማሰር ቢሞክርም ያልተሳካለት ወያኔ አሁን ግን እሳቸውን ብቻ ሳይሆን በግሉ ዘርፍ አሉ የሚባሉ የተሳካላቸውን ባለሙያዎች ጠቅልሎ እስር ቤት ለመክተት ጉዞውን እየጠናቀቀ ነው::

ይህንን ተከቶ የኮሚስኑን የውስጥ አደረጃጀት እና የሰው ሃይል ለማሻሻል በሚል ሰበብ በወያኔ ባለስልጣናት ላይ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን እና ሰነዶችን ያጠፋሉ የሚባሉ የሕወሓት የደህንነት አባልት በሰፊው በኮሚሽኑ ውስጥ ለመሰግሰግ የታቀደ ሲሆን ይህንንም የተመለከተ ፕሮፖዛል እንደቀረበ ለማወቅ ተችሏል:: እንዚህ ይመደባሉ የተባሉት የሰው ሃይል እጥረት ቀራፊዎች ስራቸው አስፈላጊ የተባሉ የጥቆማ ሰነዶችን በማጥፋት ጥቆማዎችን ሜዳ ላይ እንዲቀሩ ማድረግ ሲሆን ይህንን የሚያደርጉ አዳዲስ ሰራተኞች ስልጠና እየወሰዱ መሆኑ ሲታወቅ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ እጅግ አስጊ የተባለ ባለስልጣን ካልተፈጠረ በቀር የሙስና ኮሚሽን አይኖች ሁሉ ወደ ግሉ ዘርፍ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል::

Wednesday, August 28, 2013

Wednesday, August 28, 2013

No comments: