sourse http://ethioforum.org/
(ኢ.ኤም.ኤፍ) የዞን 9 ጦማርያን ከታሰሩ ሶስት ሳምንት ሞላቸው። እንደወንጀል የተከሰሱበት ዋና ምክንያት በውጭ አገር ድረ ገጾች ላይ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው ነው። ከቤተሰብ እና ጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተደርገው ነው የፖሊስ ምርመራ የተደረገባቸው። በዚህም ምክንያት ጠበቆቻቸው እራሳቸውን ከጥብቅና የሚያነሱ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ለመግለጽ ማሰባቸውን በይፋ ተናግረዋል። ዛሬ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ምን እንደሚሉ እና ምን እንደሚባሉ ትንሽ ቆይተን የምናውቀው ይሆናል። ከአዲስ አበባ የደረሰን መልዕክት እንደሚያስረዳው፤ ጦማርያኑፒያሳ የሚገኘው አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት ተገኝተዋል።
አሁን የደረሰን ዘገባ ከሆነ የቀረበባቸው ክስ “ማህበራዊ ድረ ገጽ (soial Media) በመጠቀም በአገሪቱ ውስጥ ብጥብጥ ለማንሳት አቅደዋል” የሚል ነው። ፖሊስ ምርመራዬን አላጠናቀቅኩም በማለት ተጨማሪ 28 ቀን እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ተፈቅዶለታል። ጦማሪዎቹ የዋስ መታቸው ተጠብቆ እንዳይወጡ ፖሊስ ጠይቋል። ይህም ተቀባይነት አግኝቶ የዋስትና መብታቸው ተነስቷል። እናም በተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ እና ዘላለም ክብረት ላይ ተጨማሪ 28 ቀን ታስረው እንዲመረመሩ ተብሏል። ቀጣዩ ቀጠሯውቸውም ለሰኔ 7 ተቀጥሯል። ነገ እሁድ ደግሞ ማህሌት ፋንታሁ፣ በፍቃዱ ሃይሉ እና አቤል ዋበላ በዚሁ የአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት ይቀርባሉ። ዳኛው ከዛሬው የተለየ ነገር እንደማያረጉና ፖሊስ የጠየቀውን ያስፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዞን ዘጠኝ የሚለውን ስያሜ ለማግኘት መነሻ የሆናቸው… ጋዜጠኛ ርእዮትን ቃሊቲ ለመጠየቅ በሄዱበት ወቅት ነው። ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የታሰረችው በቃሊቲ የመጨረሻው ዞን ውስጥ ነው – ዞን 8 ይባላል። እነዚህ ወጣቶች ሊጠይቋት ሄደው ሲገናኙ፤ “ዞን ዘጠኝ እንዴት ነው?” አለቻቸው።
ወጣቶቹም “ዞን ዘጠኝ ደግሞ የት ነው?” ይሏታል።
ርዕዮትም “ዞን ዘጠኝማ ከቃሊቲ ውጪ የሚገኘው በቁሙ የታሰረው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው” ትላቸዋለች። በነገሩ እውነትነት የተስማሙት ወጣት ጋዜጠኞች ከቃሊቲ መልስ ዞን 9 የሚል ስያሜ ያለው ብሎግ ላይ ሃሳባችወን መጻፍ ይጀምራሉ። እናም ልክ የዛሬ 3 ሳምንት የኢህአዴግ ደህንነቶች እነዚህን ወጣቶ ከየቤታቸው እየለቀሙ ወስደው አሰሯቸው። ዛሬ ፍርድ ቤት ገብተው ሲወጡ የሚደርሰንን ዘገባ በኋላ ላይ እናካፍላችኋለን። እስከዚያው ድረስ ግን ስለጦማርያኑ የዞን 9 ብሎግ ያወጣውን መግለጫ (ለግንዛቤም ይረዳል) እናስነብባቹህ። እንዲህ ይላል…
ከታሰሩ 22 ቀናትን ያስቆጠሩት የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች በቤተሰብም ሆነ በሕግ ባለሞያ የመገናኘት መብታቸውን ለማግኘት 19 ቀናትፈጅቶባቸዋል፡፡ ከታሰሩ እስከ 17 ቀን ድረስ ማንም የቤተሰብ አባል ሳይጎበኛቸውና በወዳጅ ዘመዶች ሳይጠየቁ የከረሙ ሲሆን ከጠበቆች ጋርለመገናኘት ደግሞ 19 ቀናት ፈጅቷል፡፡ አሁንም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ ቀሪ እስረኞች አሉ፡።
በተለምዶው እነደሚደረገው የፓሊስ ማእከላዊ ምርመራ የቤተሰብ ጉብኝትን አይቻልም በሚል ቀላል ቃል የከለከለ ሲሆን ለጠበቆች ስብሰባ ላይነን የሚል ምክንያት ሲሰጥ ከርሟል፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ የተያዙ ሰዎች መብት የሆነው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ሁለት ላይ ያለው የተያዙሰዎች ያለመናገር መብት ( the right to remain silent) በይፋ ተጥሶ ያለማንም የህግ ባለሞያ ምክር ለብዙ ቀናት ምርመራ ሲደረግባቸውቆይቷል፡፡
ምርመራቸውን ጨርሰዋል ተብለው የታሰቡ ታሳሪዎቸን ካልሆነም በስተቀር በምርመራ ወቅት የህግ ባለሞያ ለማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡ መሰረቱ መሰረታዊ የሆነው ያለመናገር መብትና የሕግ ባለሞያ የማግኘት መብት መከልከሉ የተለመደውን ማእከላዊ ምርመራ የሚታማበትንየማስገደድ ምርመራ እውነተኛነት የሚያጋልጥ ነው፡፡ በተጨማሪም የአካልና የስነልቦና ጉዳት የማድረስ ምርመራ ሲፈጸምባቸው እነደነበረ የተያዙየዞን ዘጠኝ አባላት በተናገሩበት ወቅት ፍርድ ቤቱ የነዚህን ጉዳቶች መከልከል ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጪ ይሄ ነው የሚባል እርምጃ እናማጣራት ለመውሰድ አልሞከረም፡፡
ማዕከላዊ ምርመራ ከዚህ በፊት የሚታወቅበት ድብደ ባ፣ ምግብና እንቅልፍ መከልከል፣ የስነልቦና ጫና እና ማስፈራሪያ የተለያዩ ዛቻዎችሁሉም በተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በተለያየ መልኩ እነደደረሰ ተረድተናል፡፡ ይህም ምርመራውን ተከትሎ የሚመጣውንማንኛውንም ማስረጃ በሕግም በሞራልም ተቀባይነት እነዳይኖረው እነደሚያደርግ እናውቃለን፡፡
ከታሳሪዎች የሚገኙ ማንኛውም መረጃዎች በከፍተኛ ተጽእኖ ስር እንደተሰጡ አንዲሁም ዝም የማለትና የሕግ ባለሞያ ምክር የማግኘት ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው የተገኙ እንደሆኑ ዞን ዘጠኝ ያምናል፡፡
በወንጀል ህግ ስነስርአት መሰረትእነዚህ ያለህግ ባለሞያ ጉብኝትያለመናገር መብታቸው (የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19) ተጥሶ የተገኙ መረጃዎች በዚህ ምክንያት ብቻ ተቀባይነት እነደማይኖራቸውም የአገሪትዋሕግ ይደነግጋል፡፡
በመሆኑም መንግስት ታሳሪዎቹን አንደፈታ እና ጉዳያቸው ሕገ መንግሰታዊ እና የወንጀል ህግ ሥነ-ስርአት ሕጉን ተከትሎ አንዲሆን እንዲያደርግናሌሎች እንዲያከብሩ የሚጠይቀውን ሕግ መንግስት ራሱን በማክበር አንዲጀምር አሁንም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡
ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ ማእከላዊ ምርመራ የሚገኙ የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ያለንን ክብር እና ፍቅር እየገለጽንጽናታቸው አስተማሪ ሲሆን በሚከተሉት ቀናት በሚኖሩት ማንኛውም የህግ ሂደቶች ውስጥ የሚኖሩትን አዳዲስ መረጃዎች ለዞን ዘጠኝ ነዋሪያንእንገልጻለን፡፡ነገ ቅዳሜ ግንቦት 9 እና እሁድ ግንቦት 10 የሚደረጉ የፍርድ ቤት ሄደቶችን አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ጠዋትበመገኘት መከታተልና አጋርነታችሁን ማሳየት ትችላላችሁ፡፡
የዞን ዘጠኝ ስብስብ አባላቶቹ ምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደማያውቁ በድጋሚ ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡
No comments:
Post a Comment