Monday, May 5, 2014

Hiber Radio: ዶ/ር ኑሮ ደደፎ ‘በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዘን ለጸረ ወያኔ ትግል እንነሳ’ አሉ፤ ሞረሽ የተማሪዎቹን ግድያ አወገዘ

 | 

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 26 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<...የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ መብት ጥያቄ ነው..ኢትዮጵያውያን ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ሰለባ ሳይሆኑ በጋራ ይንን ስርዓት መጣል አለባቸው ዛሬ ኦሮሞው ሲበደል የአማራ ተማሪዎች ዝም ማለት የለባቸውም ሌላውም እንዲሁ...>>
ዶ/ር ኑር ደደፎ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የኢንፎርሜሽን ጉዳይ ሀላፊ
<...ሞረሽ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግድያ ያወግዛል..ተማሪዎቹም የምንሊክ ሐውልት ይፍረስ ማለታቸውን ትተው ኢትዮጵያውያንን እርስ በእርስ በማተራመስ ሲፈልግ ትግራይን ለመገንጠል የሚያስበውን ህወሃትን ከሌሎች ጋር በጋራ መታገል አለባቸው..በተረፈ እንቅስቃሴው የ1960ዎቹን የተማሪዎች እንቅስቃሴ ያስታውሳል...>
አቶ ተክሌ የሻው በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የህወሃት አገዛዝ የወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ የሞረሽን አቋም በተጠየቁበት ወቅት ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የጆን ኬሪ መግለጫ፣ የታሰሩ ጋዤጠኞችና ጦማሪያን ጉዳይ ሲዳሰስ(ልዩ ዘገባ)
በኦሮሚያ የተወሰደው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዓለም አቀፍ ዘጋቢያን እይታ (ልዩ ጥንቅር)
ሌሎችም ዝግጅቶች፡
ዜናዎቻችን
* የኦነግ ከፍተኛ አመራር ሕዝቡ በብሔር ሳይከፋፈል በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተደረገውን ግድያ አውግዞ ለጸረ ወያኔ ትግል በአንድ ላይ እንዲነሳ ጠየቁ
* አንድ ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ ምዕራባውያን ለኢትዮጵያው አገዛዝ ገንዘብ እየሰጡ የአገሪቱን ዜጎች መብት እጎዱ መሆኑን ገለጹ
* በአዲስ አበባ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ በአገዛዙ ላይ ያለውን ተቃውሞ ገለጸ
* የአሜሪካ የው/ጉ/ሚ/ር በኢትዮጵአ የነጻ ፕሬስ አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ገለጹ
* በአትላንታ ኢትዮጵያዊቷ በናይጄሪያዊ ጓደኛዋ በጥይት ተገደለች
- ገዳይ ራሱን አጥፍቷል
* በናይጄሪያ የኤርትራ አምባሳደር አስመራ ላይ በደህንነቶች መታፈናቸው ተገለጸ
* በቬጋስ የሚገኘው ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ በዓል አዲስ ወደገዛው ቤተ ክርስቲያን ተዛወረ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

No comments: