(ዘ-ሐበሻ) አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ የጠራው ሰልፍ በብዙ ወከባዎች እና እንግልቶች ቢታጀብም በሰላም መጠናቀቁን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል። “ሰልፉ እጅግ በጣም ደማቅና አስገራሚ ሰልፍ ነው !” ያሉት የዜና ምንጮቻችን “በጥይት በዱላ አይገዛም አገር፤ በጥፊ በርግጫ አይገዛም አገር፤ ፖልሲ የሕዝብ ነው !መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም፤ አትነሳም ወይ አትነሳም ይሄ ባንዲራ ያነታ አይደለም ወይ !ሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻ !” በማለት መንግስትን ሲያወግዙ ውለዋል። በተለይም ሰልፈኞቹ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ግድያም አውግዘዋል።
ከተሰሙት መፈክሮች መካከል፦
የፈሪ ዱላ ጀግና ማሰር ነው !
ልማት እያሉ ሙስና ሰሩ !
ድል የህዝብ ነው !
ድምጻችን ይሰማ !
ዛሚ ሌባ!
ተማሪዎችን የገደሉና ያቆሰሉ ለፍርድ ይቅረቡ !
ስድስቱ ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች ይፈቱ !
መግደል ይቁም !
እየገደሉ ገደሉ አሉ !
ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ !
ውሸት ሰለቸን ኢቴቪ ሌባ ህዝቡ በአንድነት ሰልፍ ካስደመጣቸው መፈክሮች ይመደባሉ :
መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም !
ውሃ ፣መብራት፣
ኔት ወርክ ፣ትራንስፖር !
ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ !
ፍራቻው ይቅር ተቀላቀሉ !
ለፍትህ ብለው ቃሊት ገቡ ! በመግደል በማሰር አይገባም አገር !
ተከበረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም ፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም ! እያለ ህዝቡ እየዘመረ ነው። ሰልፉ ተጀምሯል። መፈክሩ ደምቋል። እስክድነር፣ ርዮት ፣ አንድዋለም …እያሉ የሕሊና እስረኞቹን እየጠሩ ነው። «አሸባሪ አይደለንም !» እያሉ ነው።
«ኢትዮጵያ ካድሬዎች እንደፈለጉ የሚፈነጩባት አገር አትሂንም»፣ « አንድ ሕዝብ ነን። በቋን ቋ፣ በባህል፣ በሃይማኖት ሊከፋፍሉን ሞከር። አልተሳካም» …የመሳሰሉ መፈክሮች እየተሰሙ ነው።
No comments:
Post a Comment