Friday, May 23, 2014

የአረና አመራሮች በአዳራሽ ውስጥ ታግተዋል – ፍኖተ ነጻነት



አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሀውዜን ከተማ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከመቀሌ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደርሰው እኛ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምናደርግ ስብሰባ የሚባል ነገር የለም በማለት ወደ አዳራሹ የሚመጣውን ሰው ድንጋይ በመወርወር ስብሰባው እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባውን እንዲታደም ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ሁለት አባላት ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በመግጨት አደጋ አድርሰውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዳራሹ ውስጥ ተዘግቶብን ዙሪያውን ተከበናል ፖሊስ መቆጣጠር ስላልቻለ ተጨማሪ ኃይል ጠይቋል ሲሉ የአረና አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ ወላይታ ከተማ በተደራጁ ሰዎች ዝርፊያና ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ ለማድረስ መሞከራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡arena-structure

No comments: