Monday, May 26, 2014

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ እሳት የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ወደመ

 | 


Wolkite University
(ዘ-ሐበሻ) በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተከተ ከፍተኛ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ መውደሙን የመንግስት ሚድያዎች ዘገቡ። የመንግስት ሚድያዎቹ አደጋውን ቀለል በማድረግ በእሳት አደጋው የተጎዱ ተማሪዎች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ቢሉም የአይን እማኞች ግን የሚናገሩት በተቃራኒው ነው።
በዩኒቨርሲቲው የተነሳ የእሳት አደጋ ከሌሊቱ 10 ሰዓት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የአደጋውን መነሻ ፖሊስ እያጣራሁ ነው ብሏል።
እሳቱ በሌሊት በመነሳቱ የተነሳ በመኝታ ላይ የነበሩት ተማሪዎች ከእሳት አደጋው ለመሸሽ ሲሯሯጡ በመውደቅ፣ ከግርግዳ ጋር በመጋጨትና በድንጋጤ የመቁሰል አደጋዎች እንደደረሱባቸው የሚገልጹት ዘገባዎች ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት ከተማ አጣጥ ሆስፒታል ውስጥ የህክምና እርዳታ እየተሰጣቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

No comments: