ከዳዊት ሰለሞን
በእንቁ መጽሔት የመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ዕትም አምሳሉ ገ/ኪዳን የተባሉ ጸሐፊ ለንባብ ባበቁት ጽሁፍ መነሻነት በጅማ ዩኒቨርስቲ ሁከት ተቀስቅሶ ንበረት ሲወድም በተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት በመድረሱ ዩኒቨርስቲው በዋና አዘጋጁ ኤልያስ ገብሩ ላይ ክስ አቅርቧል በማለት አራዳ ለሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያስረዱት ረዳት ሳጅን ፍሬህይወት ሰርጸ ተጠርጣሪው ዋስትና ተከልክሎ መረጃ እስክንሰበስብ የአስራ አራት ቀን ይፈቀድልን ብለው ነበር፡፡
የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ገብሩ በበኩሉ ህገ መንግስቱ ላይ የተፈቀደውን ሀሳብን የመግለጽ መብት በመንተራስ የወጣው የፕሬስ ህግ ጋዜጠኞች ዋስትና ማግኘት እንደሚገባቸው በመደንገጉ ጉዳዩን በውጪ ሆኜ እንድከታተል ፍርድ ቤቱን እጠይቃለሁ፡፡የተከሰስኩበት ጽሁፍ የሌላ ሰው በመሆኑና ኤዲቶሪያል ላይ የወጣ ባለመሆኑ የመጽሔቱ አቋም ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡እኔ በግሌ የዚህ ጽሁፍ ተቃዋሚ ነኝ ይህንን ጽሁፍ የሚቃወም ሌላጽሁፍ አትመን አሰራጭተናል፡፡በግሌ የኦሮሞ ህዝብ ታላቅ ህዝብ እንደሆነም አምናለሁ››ብሏል፡፡
ዋስትና የሚያስከለክል ክስ ባይቀርብበትም ‹‹ፖሊስ ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ የሚያጣራው ነገር በመኖሩ የሰባት ቀን ጊዜ ፈቅጃለሁ››ያሉት ደግሞ ዳኛው ናቸው፡፡በዚሁ መሰረትም ኤልያስ ግንቦት 26/09/2006 ፍርድ ቤት ይቀርባል፡፡
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.
No comments:
Post a Comment