Saturday, May 3, 2014

አንድነት በኦሮሞ ተማሪዎችና በአምቦ ነዋሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ!! – አንድነት



አንድነት በኦሮሚያ ክልልና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የመንግስት ሐይሎች በወሰዱት እርምጃ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰው ህይወት በመቀጠፉና ብዙዎችም ለአካል ጉዳት በመዳረጋቸው የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት መወያየት የግድ መሆኑን አስምሮበታል፡፡
በተማሪዎችና በተለይም በአምቦ ከተማ ህዝብ ላይ የተፈጸመው የመብት ጥሰት ምን ያህል መሆኑን ለማወቅ በቀጣዩ ሳምንት አንድነት የራሱን ልዑክ ወደ አካባቢው እንደሚልክ አስታውቋል፡፡በተማሪዎች ላይ ግድያና የአካል መጉደል እንዲፈጸም ያደረገ ትዕዛዝ ለታጣቂዎች ያስተላለፉ ክፍሎችም በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባ አንድነት አሳስቧል፡፡
ህይወታቸው የተቀጠፈ፣አካላቸው የጎደለና ቤት ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ዜጎች ተገቢ የሆነውን ካሳ የሚያገኙበት ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲመቻችም አንድነት ጠይቋል፡፡10245296_629222183827706_5534130266258925744_n
10259995_629222177161040_5864783045872176317_n
10330239_629222240494367_7588943854168524412_n
1010858_629222200494371_7109222633184471280_n

No comments: