Saturday, May 24, 2014

Home » Religion » መታየት ያለበት: “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” (Video) መታየት ያለበት: “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” (Video)





January 24, 2014
መምህር ደረጄ ዘወይንዬ
“ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ” በሚል፦ መምህር ደረጄ ዘወይንዬ፤ በግብረ ሶዶማዊያኖች፥ ላይ ባደረገው ጥናታዊ ዳሰሳ፣ ከድምጸ ተዋህዶ የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ጋር ባደረገው የቃለ መጠይቅ ቆይታ፥ እንዴት ወደ ግብረ ሰዶማዊነት ሕይወት እንደገቡ፣ በግብረ ሰዶማዊነት ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ ሥራዎቻቸውና እንቅስቃሴዎችቸውን፤ በተመለከተ ሰፋ ያለ፥ በተበራራና ግልፅ በሆኑ ቃላቶች፣ ከግብረ ሰዶማዊያን ሕይወትና ተመክሮ በመነሳት፣ ስለ ግብረ ሰዶማውሪያን እንቅስቃሴ የሚያመለክትና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ፣ ወደዚህ ሕይወት ለገቡት የመውጪያውና የማምለጫው በር፣ ወደዚህ ሕይወት ለመግባት ዳር ዳር ላሉ ደግሞ የደውል ምልክት ነውና። ታዲያ በግብረ ሰዶማዊያን ዙርያ የቀረበው በተጨባጭ ሁናቴ በመረጃና በማሰረጃ ስለሆነ ግንዛቤ እንዳስጨበጠን የታመነ ሃቅ ነው!
“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” የሚለውን በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ አዘጋጅና አቅራቢነት በቪዲዮ ወምስል ካቀረበልን ከግብረ ሰዶማዊያን መካክል አንዱና ዋነኛ የሆነው አብይ (ኤሊያና) ስለራሱና ስለ ጓደኞቹ ስል ግብረ ሰዶማዊያን ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ በእውነተኛ ታሪካቸው በተፃፈው መፅሐፍ አማካይነት ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ሲናገር እንዲህ ነው የሚለው፦
* “ግብረ ሰዶማዊነት፥ እንደ ማግኔት ነው! አንድ ጊዜ ስቦ ካጣበቀ በኋላ የማይለቅ” ነው ብሎ ይገልፀዋል። (መፅሐፍ፦ የሰዶም ነፍሳት፥ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ)
* በዚህ ቪሲዲም ሆነ መፅሐፍ ላይ አብይ (ኤሊያና) እራሱን ትውልድ ይዳን ግብረ ሰዶማዊነት በኛ ይበቃ በማለት እራሱን አሳልፎ የገለጠ ታላቅ ሠው ነው።
* አብይ (ኤሊያና) ይሁን ሌሎችም በግብረ ሰዶማዊነት ያገኙት አንዳች ጥቅም እንደሌለ ነው የሚስረዱት።
* በግብረ ሰዶማዊነት ያገኘውና ያተረፍ ትርፍ ቢኖር፥ የሥነ-ልቦና ቀውስ፣ የህሊና ወቀሳ፣ በራስ የመተማመን ስሜት ማጣት፣ የፊንጢጣ፣ የኤች ይ ቪ ፖዘቲቭ፣ ለተለያዩ በሽታ መጋለጥ፣ ወደ ተቃራኒ ፆታ መቅረብ አለመቻል፤ እነዚህን ሌሎችንም የመሳሰሉትን ቀውሶችን ለራሳቸው ገንዘብ እንዳደረጉ እንደሆነ ነው የሚገልፁት።
* ትውልድ እስከዳነ ድረስ ሞትም ቢሆን ለእኔ ጥቅሜ ነው!!! (ለሠዎች እራሱን በመግለጡን ምክንያት ለሚመጣበት ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ሲያጠይቅ)
(ከላይ ከዕርሱ፥ እንዳነበባችሁት፣ እንዳያችሁትና እንዳዳመጣችሁ፤ እርስዎ በሃገራች ይህ መኖሩን ያውቁ ነበር? አሁንስ ምን ይላሉ? ስለ ሰዶመ ነፍሳት ምን ተሰማዎት? ምንስ ይላሉ? ከልጆዎ ጋር ስለዚህ አስከፊነት እንዴትስ ሊነጋገሩ አስቧልን? ከወዳጅ፣ ከዘመድ-አዝማድስ ጋር ሊያወሩበት ተዘጋጅተዋልን? ከባልዎ ወይንም ከሚስትዎ፣ አልያም ከፍቅር ጓደኛዎስ ጋር በግልፅ ልትነጋገሩበት ወስናችዋልን? ተወያዩበትና ወስኑ!!!)

No comments: