በኖርዌ ኦስሎ ሜይ 8 ቀን 2014 (ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ) የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ:ያደረሰውን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ :
በኦሮሚያ ክልል በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትበሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የወያኔ መንግስት ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰው ህይወት መቀጠፉና ብዙዎችም ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው ይታወቃል::
ይህንንም ተከትሎ በኖርዌ ኦስሎ ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ በኦስሎና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የድጋፍ ድርጅቱ ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ሰልፉ በተጀመረበት ቦታ በመገኛት በግፍ ለሞቱት የኦሮሞ ተማሪዎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ካደረጉ በኋላ ዘረኛውና አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ወጣት ተማሪዎች ላይ ያደረሰውን የአካል ጉዳትና ግድያ በመቃወም ድምጻቸውን አሰምታዋል ::
ሰላማዊ ሰልፉ በኖርዌ የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 15:00 ጀምሮ እስከ 17:30 የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉላይ የተገኙ ኢትዮጵያኖች በሰላማዊ መንገድ ጥያቄቸውን ሲጠይቁ በነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ጥይትን በማዝነብ ኢሰብሃዊ ድርጊት የፈጸመውንና ቡዙዎችን የገደለውን የወያኔን መንግስት የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን በማያዝ እና በማሰማት ተቃውሞቸውን በሀይል ገጸዋል:: በሰልፉ ላይ ሰልፈኞቹ ያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል የወያኔ መንግስት ገዳይ መንግስት ነው፣ የኦሮሞ ተማሪዎችን በጅምላ መግደል ይቁም፣ በኢትዮጵያ በጅምላ ስለተገደሉት የኦሮሞ ተማሪዎች አዝነናል፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣የሚሉ ይገኙበታል::
ሰልፈኞቹ በቀጥታም ወደ ኖርይጅዋያን ፓርላማ ጽህፈት ቤት በመሄድ ለኖርዌ መንግስት ጉዳዩን በግልጽ ያሳ ወቁ ሲሆን ኖርዌ ከወያኔ መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረም ጠይቀዋል:: በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ፣ ከጋራ መድረክ፣ ከስደተኞች ማህበር፣ከሸንጎ፣ከኢትዮጵያ ማህበር ኖርዌ የተገኙ መሪዎችና ተወካዪች የወያኔን ግፍ በመቃወም ንግግር አድርገዋል::በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሊቀመንበር አቶ ዮሀንስ አለሙ የድርጅታቸውን አቋም ሲገልጹ ድርጅታቸው በድርጊቱ በጣም እንዳዘነና በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑና ለሞቱ ዜጎች ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን በመመኘት የታሰሩ ወጣት የኦሮሞ ተማሪዎች በአስቸኮይ እንዲፈቱ፣ የዚህም ድርጊት ፈጻሚ አንባገነኖች በአስቸኮይ ለፍርድ እንዲቀርቡ በመጠየቅ የድርጅቱን የአቋም መልክት ለኖሮዊጅያን ምክር ቤት ተወካይ ያስረከቡ ሲሆን የምክር ቤቱም ተወካይ ንግግር አድርገው ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ሰአት ተጠናቋል::
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ sourse zhabsha
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
No comments:
Post a Comment